በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ ምርጫ ኮንግረስን ማን ይቆጣጠራል የሚለው ገና አለየለትም


የድምጽ ቆጠራ ዊስከንሰን፣ መዋውኪ
የድምጽ ቆጠራ ዊስከንሰን፣ መዋውኪ

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በቀሪው ግማሽ የሥልጣን ዘመናቸው ፖሊሲያቸውን ማስፈጸም ይችሉ እንደሁ የሚወስነው በትናንቱ ምርጫ፣ የትኛው ፓርቲ ኮንግረስን ይቆጣጠራል የሚለው ገና አልለየለትም፡፡

ይህ ሪፖርት እከተጠናቀረበት ድረስ ዲሞክራቶቹ 48 ሪፐብሊካኖቹ ደግሞ 47 መቀመጫዎችን በህግ መወሰኛው ም/ቤት አግኝተዋል ሲል ሮይተርስ አመልክቷል። ዲሞክራቶቹ አንድ መቀመጫ ነጥቀዋል።

በተወካዮች ም/ቤት ምርጫ ደግሞ ሪፐብሊካኖቹ 199 ለ173 በመምራት ላይ ናቸው።

ሪፐብሊካኖቹ ያጥለቀልቁታል ተብሎ ምርጫን በሚከታተሉ ተቋማት ሲነገር የነበረ ግምት ለግዜው በታየው ውጤት የተወሰኑ መቀመጫዎችን ብቻ በመያዛቸውና የድምጽ ቆጠራውም ገና ባለመጠናቀቁ፣ የግምቱን እውነተኝነት ለማወቅ መጠበቅ ግድ ሆኗል።

ትናንት ከተደረገው ድምጽ አሰጣጥ በተጨማሪ፣ 45 ሚሊዮን መራጮች ቀደም ብለው በፖስታ ቤት በኩልና በአካል ድምጽ የሰጡ ሲሆን፣ በዚህ ምርጫ አጠቃላይ የድምጽ ሰጪዎች ቁጥር በእአአ 2018 ከነበረው 115 ሚሊዮን ሊበልጥ እንደሚችል አንዳንድ ተንታኞች ግምታቸውን በማስቀማጥ ላይ ናቸው።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG