በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"አሁን ያለው ህገ መንግሥት ለኢትዮጵያ አንድነት ዋስትና የሚሰጥ አይደለም" - አቶ ልደቱ አያሌው


ፎቶ ፋይል፡- አቶ ልደቱ አያሌው
ፎቶ ፋይል፡- አቶ ልደቱ አያሌው

አሁን ያለው ህገ መንግሥት ለኢትዮጵያ አንድነት ዋስትና የሚሰጥ አይደለም ሲሉ አንድ የቀድሞ የተቃዋሚ መሪና የፓርላማ አባል ተናገሩ፡፡ ህገ መንግሥቱ ለፌዴራሊዝም ሳይሆን ለኮንፌዴሬሽን ወይም ለመነጣጠል የሚሆን ነው ሲሉ ነው የተቃዋሚው መሪው አቶ ልደቱ አያሌው ለአሜሪካ ድምፅ የገለፁት፡፡

ቀጣዩን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ የሀይል አሰላለፍ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል የጠቆሙት አቶ ልደቱ መንግሥቱን ለማሻሻል የተሻለው አጋጣሚ፣ ይህ የሽግግር ወቅት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉት ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ህገ መንግሥቱን የማሻሻል ጉዳይ ለውይይት ዝግ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ይህ መሆን ያለበት ግን የቀደመውን፣ የማፅደቅ ሂደት ችግር በማይደግምና ሁሉንም ህዝቦች ባሳተፈ መንገድ እንደሆነ ነው የሚያብራሩት፡፡

ተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

"አሁን ያለው ህገ መንግሥት ለኢትዮጵያ አንድነት ዋስትና የሚሰጥ አይደለም" - አቶ ልደቱ አያሌው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:56 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG