በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የስደት ኑሮ ክህሎት አሠልጣኟ የቀድሞ ስደተኛ


የስደት ኑሮ ክህሎት አሠልጣኟ የቀድሞ ስደተኛ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:46 0:00

የስደት ኑሮ ክህሎት አሠልጣኟ የቀድሞ ስደተኛ

ከተወለዱበት ካደጉበት ሀገር ወጥቶ ከቤተሰብ እና ከጓደኛ ተለይቶ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መምጣት ምን እንደሚመስል ኩርዳዊቱ ሳይራን አግራዊ ኖራዋለችና በሚገባ ታውቀዋለች። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1997 ዓ.ም ከኢራቅ ወደ አሜሪካ የመጣችው ሳይራን እሷ ባለፈችበት ፈታኝ ጎዳና ሌሎች እንዳያልፉ መርዳት ላይ ተሰማርታለች፡፡

የሚደቀኑባቸውን ከባድ ፈተናዎች ተቋቁመው ወደተሻለ ኑሮ ለመሸጋገር እንዲችሉ የሽግግር ክህሎት ሥልጠና ትሰጣለች። እናም በአሁኑ ወቅት ሳይራን ወደዩናይትድ ስቴትስ የሚመጡ የውጭ ሀገር ሰዎች ከኖሩበት የሀገራቸው ባህል የተለየ በሆነው ባህል እንዳይደናገጡ እና ቋንቋውንም እንዲማሩ ትረዳለች፡፡

ሳይራንን ከሁሉም የሚያስደስታት አዲሱን ሀገራቸውን ለምደው አገሬ ብለው ተመችቷቸው ሲኖሩ ማየት መሆኑን ትናገራለች።

የቪኦኤዋ ሊሳ ቮራ ከቨርጂኒያ ጌይንስቪል ከተማ ያጠናቀረችው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG