በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሸርማን - አሜሪካ የኤርትራን ተቃዋሚዎች መርዳት አለባት


የዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤት አባል ብራድ ሸርማን
የዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤት አባል ብራድ ሸርማን

የዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤት አባል ብራድ ሸርማን አሜሪካ ከኤርትራ ተቃዋሚ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ማድረግ እንደሚያስፈልጋት አፅንዖት ሰጥተው ተናገሩ፡፡

ዴሞክራቱ የምክር ቤት አባል ይህን የተናገሩት ከመስከረም አሥራ አንዱ የሽብር ጥቃት ጋር በተገናኘ በምክር ቤቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በአፍሪካ ኃያላን መንግሥታት የያዙትን ፉክክር አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት በምክር ቤቱ በተካሄደ የምስክነት ቃል በተሰማበት ወቅት ነው፡፡

ሸርማን በዚሁ ወቅት በሰጡት አስተያየት “የኤርትራ ሕዝብ ነጻነት የለውም፣ በኤርትራ ዴሞክራሲያው መንግሥት እስክናይ ድረስ የኤርትራ ጎረቤቶች ሰላም አይኖራቸውም” ብለዋል፡፡

የካሊፎርኒያው ተወካይ ሸርማን “በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ላይ ጥቃት የፈጸሙ” ያሏቸውን የኤራትራውን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን “የሰሜን አፍሪካዋ ሰሜን ኮሪያ ተብሎ በትክክል ሊጠራ የሚችል መንግሥት ፈጥረዋል” ሲሉ ነቅፈዋቸዋል፡፡

ስለጉዳዩ የተጠየቀው የኤርትራ መንግሥት "ስለ አካባቢው ታሪክ እና ወቅታዊ እውነታ ምንም ፍንጭ የሌላቸው፣ ሼርማን ስለ ኤርትራ ህዝብ ነፃነት"የመናገር ግን ድፍረቱ አላቸው" ሲል ትችቱን አጣጥሏል፡፡

ከስነምግባር/ህጋዊነት እና ከክልሉ ህዝቦች ደህንነት ጋር ምንም ግንኙነት አልነበረውም። "

ሸርማን በኤርትራ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ለማምጣት የአሜሪካ ድጋፍ እንዲጠናከር ጠይቀዋል።

“በቅርቡ ከተቃዋሚው ፓርቲ መሪ ከአቶ ገብረ ባዱራይ ጋር ተገናኝቻለሁ” ያሉት ሸርማን “የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ በዓለም ዙሪያ ኤርትራ ውስጥ የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲኖር ከሚሰሩት እና በዓለም ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ እንዲኖር ከሚሰራ መንግሥት ጋር አብሮ ይሰራል ወይ?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ጥያቄው የቀረበላቸውና ለምስክርነት የቀረቡት በዩናትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ሚንስትሩ ጆን ባስ ኤርትራ በአብዛኛው ከነጻነት በኋላ የረዥም ጊዜ የጭቆና ታሪክና ብቻውን የተነጠለ መንግሥት ያላት ሀገር ናት” ብለዋል፡፡

ባስ አክለውም “ብዙ ጊዜ እነዚያ ሁኔታዎች እንዲለወጡና ለማህበረሰቡ ሁኔታዎች ክፍት እንዲሆኑ በእኛ እና በአጋሮቻች የተደረጉ ጥረቶችን ችላ ይላሉ” ሲሉ ስለኤርትራው ፕሬዝዳንት ተናግረዋል፡፡

“በዚህ ልዩ ጉዳይ ላይ የምንከተለውን ፖሊሲ አስመልከቶ ያሉንን ምላሾች ይዥ እመለሳለሁ” ያሉት ባስ አቅማችንን ሙሉ በመጠቀም መንግሥትን በንቃት ማስተፋችንን እንደምንቀጥልም አረጋግጥልዎታለሁ” ብለዋል፡፡

“ፖለቲካዊ ጭቆናን እና የተቃውሞ ፖለቲካ ምህዳር አለመኖርን ጨምሮ በርካታ ችግሮችን ለመፍታት የዋለው አቅም ውስን ነው” ሲሉም አክለዋል ባስ፡፡

የምርክ ቤቱን አባል አስተያየት ተከትሎ በዋሽንግተን የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሸርማን ያለምንም ማስረጃ “ኤርትራ ለምግብ ርዳታ ወደቦቿን ዘጋች” ብለዋል ሲል አስተያየታቸውን ነቅፏል፡፡

እኤአ በ2000 የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በተፋፋመበት ወቅት እንኳ ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ ሰብአዊ ርዳታዎች የአሰብና ጅቡቲ ወደቦችን ማቅረቡን መግለጫ ጠቅሷል፡፡

“ኤርትራ መቼም ቢሆን የሰብአዊ ርዳታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ አላገደችም እንቅፋትም አልሆነችም” ያለው መግለጫ “እስከ አሁን ድረስ ኤርትራ በወደቦቿ በኩል የምግብ ዕርዳታ እንድትሰጥ ለምን አልተጠየቅችም” ሲል ጠይቋል፡፡

መግለጫው አክሎም “ኤርትራ የአሜሪካ እርዳታ ተቀባይ ሀገር ስላለሆነች ለኢኮኖሚ ጫና የተጋለጠች አልሆነችም” ሲል ይልቁንም የምክር ቤት አባሉ ዩኝትድ ስቴትስ ህገወጥ የኃይል እርምጃ እንድትወስድ ምክንያቶችን እያወሳሰቡ መሆኑን በመጥቀስ ነቅፏል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG