አዲስ አበባ —
ኤችአር 128 ተብሎ የሚታወቀውን የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ቀደም ሲል ባሳለፈው የሰብዓዊ መብቶችና የተጠያቂነት ሕግ ላይ ከተቀመጡት አንቀፆች አንፃር በሀገሪቱ ያለውን መሻሻል ለባልደረቦቻቸው እንደሚያስረዱ ኢትዮጵያ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች አስታውቀዋል፡፡
ሪፖብሊካኑ ክሪስ ስሚዝና ዴሞክራቷ ኬሬን ባስ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ በሰጧቸው መግለጫዎች የ/ኤችአር 128/ ቀጣይ ሂደት የሚታወቀው ወደ ዋሺንግተን ከተመለሱ በኋላ በሚደረጉ ውይይቶች እንደሆነ ነው የጠቆሙት፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ