በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት አስተዳደር በአሜሪካ የኮንግረስ አባላት ፊት ተተቸ

ለምስክር ሰሚ ሸንጎ ቀርበው ምስክርነታቸውን የሰጡት ስድስት ሰዎች የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎቹን "ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብት ይጥሳል። ከአሜሪካ በእርዳታ የወሰድውን ገንዘብ ለፖለቲካ ፍጆታው መጠቀሚያ ያውለዋል” ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሰጠው የገንዘብ እርዳታ ለታሰበለት ዓላማ መዋሉን፣ ከአሜሪካ ጋር የሚኖራት የንግድ ግንኙነት እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለው የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ይዞታ ትኩረት እንዲደረግበት ለሚጠይቀው በኮንግረስ አባላት ለቀረበው “ሪዞሊሽን 128” የፖለቲካ ተንታኝ፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ተወካይ እና አራት ኢትዮጵያውያን ለዩናይትድ ስቴስት ምክር ቤት የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ አባላት ምስክርነታቸውን ሰጥተው ነበር።

ለምስክር ሰሚ ሸንጎ ቀርበው ምስክርነታቸውን የሰጡት ስድስት ሰዎች የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎቹን "ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብት ይጥሳል። ከአሜሪካ በእርዳታ የወሰድውን ገንዘብ ለፖለቲካ ፍጆታው መጠቀሚያ ያውለዋል” ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

ለምስክር ሰጪዎች ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጽዮን ግርማ ይህንን የተመለከተ ዝርዝር ዘገባ ይዛለች።

የኢትዮጵያ መንግሥት የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት አስተዳደር በአሜሪካ የኮንግረስ አባላት ፊት ተተቸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:45 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG