በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ም/ቤት ጥሪ አቀረበ


በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ም/ቤት ጥሪ አቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:33 0:00

በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ም/ቤት ጥሪ አቀረበ

የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ኢትዮጵያን በተመለከተ ተሻሽሎ የተዘጋጀ የተባለውን የውሳኔ ሐሳብ አጽድቋል፡፡

ለግጭቱ ፖለቲካዊ መፍትሔ ለማምጣት፣ መንግሥት ከሕግ ውጭ የታሰሩ የተቃዋሚ መሪዎችን እና ደጋፊዎችን፣ ተሟጋቾችና ጋዜጠኞችን እንዲፈታ እንዲሁም ከአመጽ ውጭ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ የተለያዩ አካላትን ያሳተፈ ብሔራዊ ውይይት እንዲያደርግ የውሳኔ ሐሳቡ ጠይቋል፡፡

የውሳኔ ሐሳቡ መጽደቁን ተከትሎ በምክር ቤቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ፤ የአፍሪካ፣ የዓለም ጤና እና የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ኬረን ባስ፣ በሰጡት መግለጫ ህወሃት ህጻናትን ለጦርነት መጠቀምን እንዲያቆም፣ ከአማራ ክልል ኃይሉን እንዲያስወጣ እና ከሸኔ ጋር ያለውን ጥምረትም እንዲያቆም አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG