የኩባያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴኒስ ምዩለንበርግ በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ፊት ቀርበው ትናንትና ትናንት ሲጠየቁ ስሕተትና ጥፋት መፈፀሙን አምነው “እኔም ልቤ ተሰብሯል፤ በጥልቅ አዝናለሁ” ብለዋል።
የኩባንያቸው መታመን እንደገና እንዲያንሠራራ ለማድረግ በርትተው እንደሚሠሩና እንዲያ ዓይነት ጥፋት እንደማይደገምም ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የንግድ፣ የሣይንስና የትራንስፖርት ኮሚቴ ተናግረዋል።
የተጎጂዎች ቤተሰቦችና የሕግ ተወካዮቻቸውም ተገኝተዋል።
የቦዪንግ ከፍተኛ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ዛሬም በተወካዮች ምክር ቤቱ የትራንስፖርት ኮሚቴ ፊት ቀርበው ተጠይቀዋል።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ