በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮንጎ ፕሬዚዳንት ለተጨማሪ አምስት ዓመት በድጋሚ ተመረጡ


ፎቶ ፋይል፦ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱ ኑጉዌሶ
ፎቶ ፋይል፦ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱ ኑጉዌሶ

ለበርካታ ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆዩት የኮንጎው ፕሬዚዳንት ለተጨማሪ የአምስት ዓመት የሥልጣን ዘመን በከፍተኛ ድምፅ ተመረጡ።

በኮንጎ ሪፖብሊክ ለበርካታ ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱ ኑጉዌሶ ተጨማሪ የአምስት ዓመት በከፍተኛ ድምፅ ማሸነፋቸውን የአገር ደህንነት ሚኒስትሩ አስታወቁ።

ሬይመንድ ዜፊሪ ሙቡሎ ትናንት ባደረጉት ንግግር ሳሱ ንጉዌሶ እሁድ እለት ከተሰጡት ድምጾች ውስጥ ሰማኒያ ስምንት ከመቶውን አግኝተው፣ ለሰላሳ ስድስት ዓመታት በዘለቀው የስልጣን ጊዜያቸው ላይ ጨምረውበታል።

ድምፁ እየተሰጠ በነበረት ወቅት በድንገት ያረፉት ጊ ብሪ ፓርፌ ኮሌላ ከስምንት ከመቶ ያነሰውን ድምፅ ያገኙ ሲሆን የተቀረውን ድምጽ አምስት ሌሎች ዕጩዎች ተካፍለውታል።

የኮሌላ ቃል አቀባይ እንዳሉት ፕሬዚዳንታዊ ዕጩ ተፎካካሪው ህይወታቸው በኮቪድ ምክንያት ያለፈው ከብራዛቪል ለህክምና ወደፈረንሳይ እየተወሰዱ ሳሉ ነው።

XS
SM
MD
LG