በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ድጋሚ ለመመረጥ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ

የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ
የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ

የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ድጋሚ ለመመረጥ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ። በመጪው ምርጫ የቀድሞ የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ኢማኑኤል ራማዛኒ ሻዳሪን ዕጩነት እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።

የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ድጋሚ ለመመረጥ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ። በመጪው ምርጫ የቀድሞ የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ኢማኑኤል ራማዛኒ ሻዳሪን ዕጩነት እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።

ይህን ዛሬ ይፋ ያደረጉት የኮንጎ መንግሥት ቃል አቀባይ ላምበርት መንዴ ሲሆኑ ጉዳዩ ይፋ መሆኑ ሚስተር ካቢላ ህገ መንግሥቱ ሁለት የሥልጣን ዘመን ብቻ ቢፈቅድም ለሦስተኛ የሥልጣን ዘመን ሳይወዳደሩ አይቀሩም ተብሎ ለዓመታት የቆየውን ጥርጣሬ አክትሞታል።

እኤአ በሚቀጥለው ታኅሣስ ሃያ ሦስት ለሚለየው ፕሬዚዳንታዊ ውድድር ዕጩዎች የነበራቸው የመመዝገቢያ ቀነ ገደብ ዛሬ ከቀትር በኋላ አብቅቷል።

ካቢላ ሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው አብቅቶ ከመንበሩ መውረድ የነበረባቸው ባለፈው 2016 መጨረሻ ሲሆን ህገመንግሥታዊ አንቀጽ ጠቅሰው በተጠባባቂነት እስከ አሁን ቆይተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG