በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ በሚካሄደው ዘር ተኮር ግጨት ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቀሉ

በኮንጎ ዲሞራስያዊ ሪፖብሊክ ሰሜን ምሥራቅ የሚካሄደው ዘር ተኮር ግጭት በአስር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ስዎችን ከመኖርያቸው አፈናቅሏል። ወደ 50ሺሕ የሚጠጉት ወደ ኡጋንዳ ጎርፈዋል።

በኮንጎ ዲሞራስያዊ ሪፖብሊክ ሰሜን ምሥራቅ የሚካሄደው ዘር ተኮር ግጭት በአስር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ስዎችን ከመኖርያቸው አፈናቅሏል። ወደ 50ሺሕ የሚጠጉት ወደ ኡጋንዳ ጎርፈዋል።

በደካማ ጀልባዎች አልበርት ሃይቅን አቋርጠው ኡጋንዳ ለመግባት በሚያደርጉት ጉዞ ለሞት የተዳረጉ ብዙ ስደተኞች እንዳሉ ታውቋል። ጉዞው አምስት ሰዓታት ይወስዳል።

በኮንጎው ኢቱሪ ክፍለ ሀገር ከሚካሄደው ዘር ተኮር ግጭት ነው የሚሸሹት አብዛኞቹ ሰደተኞች፣ ጥቂት ንብረቶች ይዘው የወጡ መሆናቸዋንና ብዙዎቹ የጠፉ ልጆቻቸውንና ዘመድ አዝማድን እየፈለጉ መሆናችውን ሰደተኞቹ ተናግረዋል። ዱኒሲክወቱ ሶሮንጋኒ የተባሉ ሰው ለአንድ ወር ያህል ባለቤታቸውን ለማግኘት አለመቻላቸውን ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG