በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንታዊው ተፎካካሪ በኮቪድ ህይወታቸው አለፈ


ፎቶ ፋይል፦ የኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዋናው ተቃዋሚ ተፎካካሪው ጊ ብሪ ፓርፌ
ፎቶ ፋይል፦ የኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዋናው ተቃዋሚ ተፎካካሪው ጊ ብሪ ፓርፌ

የኮንጎ ብራዛቪሉ ዕጩ ፕሬዚዳንታዊ ተፎካካሪ በኮቪድ 19 ምክንያት አረፉ። በመጪው የኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዋናው ተቃዋሚ ተፎካካሪው ጊ ብሪ ፓርፌ ኮሌላ በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ተዘገበ።

የኮሌላ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ተቃዋሚ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩው በተወለዱ በስድሳ አንድ ዓመታቸው ትናንት ዕሁድ ህይወታቸው ያለፈው ለህክምና ከብራዛቪል ወደፈረንሳይ በመወሰድ ላይ እንዳሉ ነው። ኮሌላ ትናንት ዕሁድ ለተካሄደው ምርጫ የመጨረሻ በነበረው በአርቡ የመጨረሻ የምረጡን ዘመቻ ላይ በጸና በመታመማቸው የተነሳ ሊካፈሉ አልቻሉም ነበር።

ሆኖም ቅዳሜ ዕለት ከሆስፒታል አልጋቸው ላይ ሆነው ለደጋፊዎቻቸው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት የኦክሲጂን ማገዣ ማስክ በእጃቸው ይዘው እያሳዩ "እኔ ከሞት ጋር እየታገልኩ ነኝ፤ እናንተ ግን ለለውጥ ቆማችሁ ድምጻችሁን ስጡ" ሲሉ ሲማጸኑ ተደምጠዋል።

እአአ በ2016 ከፕሬዚዳንቱ ዴኒስ ሳሱ ኑጉዌሶ ጋር ተወዳድረው በሁለተኛነት የጨረሱት ኮሌላ በዚህኛው ምርጫ ለሁለተኛ ጊዜ መወዳደራቸው ነበር።

የትናንቱ ምርጫ ውጤት ይፋ እስከሚደረግ በርካታ ቀናት ይወስዳል ተብሏል። ሆኖም ታዛቢዎች የሰባ ሰባት ዓመቱ ሳሱ ንጉዌሶ እንደሚያሸንፉ እና ሥልጣናቸው ላይ ይቆያሉ ብለው ይጠብቃሉ።

ሳሱ ንጉዌሶ መጀመሪያ ላይ እአአ በ1979 ሥልጣን ይዘው እስከ 1992 ከአስተዳደሩ በኋላ ከዚያ በኋላ ደግሞ እአአ ከ1997 ጀምረው ያለማቋረጥ ሥልጣን ላይ ቆይተዋል።

XS
SM
MD
LG