በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በመራጮች ምዝገባው ለገዢው ፓርቲ አድልዎ እየተደረገ ነው” የኮንጎ ተቃዋሚ ፓርቲዎች


መራጮች ምዝገባ እያደረጉ፤ 2/16/2023
መራጮች ምዝገባ እያደረጉ፤ 2/16/2023

በመጪው ታህሳስ ኮንጎ ውስጥ ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ ያለው የመራጮ ምዝገባ መዘግየቱን በሚመለከት አንዳንዶቹ ተቃዋሚ ዕጩዎች እሮሮ እያሰሙ ናቸው፡፡ የመራጭ ምዝገባ ዘመቻው እኛን በሚጎዳን የተዛባ መንገድ እየተካሄደ ነው ሲሉ ወጅለዋል፡፡

እአአ እስከመጪው መጋቢት 17 ቀን ድረስ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች እንዲመዘገቡ ታቅዶ ነበር፡፡ ሆኖም የምርጫ ኮሚሽኑ ባለፈው አርብ በሰጠው መግለጫ በዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ያሉትን ጨመሮ ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ የመራጭ ምዝገባ ማዕከላት ካሁን ቀደም የጊዜ ገደቡ በ25 ቀናት ቢራዘምም ምዝገባቸውን እንዳላጠናቀቁ አመልክቷል፡፡

ኪንሻሳ ክፍለ ሀገር የሚገኙ 24 የምዝገባ ማዕከላት እና በማዪ ኢንዶቤ ያሉ ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ ጣቢያዎች ደግሞ በጸጥታ ችግር የተነሳ አለመከፈታቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ገልጸዋል፡፡

የተቃዋሚ ዕጩ የሆኑት ማርቲን ፋዩሉ በምርጫ ኮሚሽኑ ካርታ ላይ ያሉ ያልተከፈቱ ጣቢያዎች እንዲሁም መከፈት ሳይኖርባቸው የተከፈቱ ጣቢያዎች እንዳሉ አመልክተዋል፡፡ የምርጫ ኮሚሽኑ ለማጭበርበር እንዲመች ትርምስ እንዲፈጠር እያደረገ ነው በማለት ተቃዋሚው ዕጩ ወንጅለዋል፡፡

እሳቸው እና ሌላው የተቃዋሚ ዕጩ ሞኢዚ ካቱምቢ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል ኮሚሽኑ የፕሬዚዳንት ፌሊክስ ቲሼኬዲ የትውልድ ክፍለ ግዛት ካሳይን ለመሳሰሉ ለፕሬዚዳንቱ ታማኝ ለሆኑ አካባቢዎች ቅድሚያ እየሰጠ ነው በማለት ከስሠዋል፡፡

ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሶስት ኮንጎአዊ እና ዓለም አቀፍ የምርጫ ኤክስፐርቶች ለሮይተርስ በሰጡት ቃል የፕሬዚዳንት ቲሺኬዲ እና የተቃዋሚዎች ደጋፊዎች ለሆኑ አካባቢዎች በተሰጡት የምዝገባ ቁሳቁስ ቁጥር የተዛባ ሁኔታ ማስተዋላቸውን አመልክተዋል፡፡ የምርጫ ኮሚሽኑ አስካሁን መልስ አልሰጠም፡፡

ተደማጭነት ያለው የካቶሊክ እና የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት የምርጫ ታዛቢ ሚሽን አርብ በሰጠው መግለጫ ኮሚሽኑ ስለጉዳዩ ረጋ ብሎ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ተስፋ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

ባለፉት ሁለቱ ሳምንታት ውስጥ የምዝገባ ቁሳቁስ መዘግየት የምዝገባ መሳሪያዎች ብልሽት የመሳሰሉ 200 ችግሮችን ማየቱን የአብያተ ክርስቲያኑ ታዛቡ ቡድን አስታውቁዋል፡፡

XS
SM
MD
LG