በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምሥራቅ ኮንጎ ፍንዳታ 11 ሰዎች ሞቱ

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ክፍል የአማጺው ኤም 23 መሪዎችና ነዋሪዎች ሰልፍ ማድረጋቸውን ተከትሎ በተከሰተ ፍንዳታ 11 ሰዎች ሲሞቱ 65 የሚሆኑ ተጎድተዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች የተጋሩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች በርካታ ሰዎች ሲሸሹ እና በደም የተለወሱ አስከሬኖችም መንገድ ላይ ወድቀው አሳይተዋል።

ፍንዳታዎቹ በተከሰቱበት ወቅት የኤም 23 መሪዎች በማዕከላዊ ቡካቩ ከተማ ከነዋሪዎች ጋራ ውይይት በማድረግ ላይ ነበሩ።

ፍንዳታው “የሽብር ሥራ እና በሕገ ወጥ መንገድ በኮንጎ በሚገኝ የውጪ ጦር የተፈጸመ ነው” ሲሉ የኮንጎ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቺሴኬዲ ክስ አሰምተዋል።

ኤም 23 በበኩሉ "የኮንጎ ባለሥልጣናት ፍዳታውን አቀናብረዋል" ሲል ከሷል። “የኪንሻሳው አገዛዝ ሲቪሎችን ለማጥፋት ተነስቷል” ሲልም አክሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG