በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮንጎ ምርጫ


ጆዜፍ ካቢላ
ጆዜፍ ካቢላ

ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ውስጥ ከነገ በስተያ - ዕሁድ ይካሄዳል ለተባለው ምርጫ ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑንና ፀጥታና ደኅንነቱም ሙሉ በሙሉ እንደሚጠበቅ ፕሬዚዳንቱ ጆዜፍ ካቢላ ዛሬ አስታወቁ።

ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ውስጥ ከነገ በስተያ - ዕሁድ ይካሄዳል ለተባለው ምርጫ ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑንና ፀጥታና ደኅንነቱም ሙሉ በሙሉ እንደሚጠበቅ ፕሬዚዳንቱ ጆዜፍ ካቢላ ዛሬ አስታወቁ።

ምርጫው ለምን ላይካሄድ እንደሚችል አንዳችም ምክንያት አይታየኝም ብለዋል ፕሬዚዳንት ካቢላ ከቪኦኤ ጋር ዛሬ በደረጉት ቃለ-ምልልስ።

ባለፈው ዕሁድ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ፕሬዚዳንታዊና የፓርላማ ምርጫ ዋና ከተማዪቱ ኪንሻሳ ውስጥ በሚገኝ መጋዘን ላይ በተነሣ እሳት የምርጫ መሣሪያዎችና ቁሣቁስ በመቃጠላቸው ለአንድ ሣምንት ተገፍቶ ነው ወደ ከነገ-በስተያ የተዛወረው።

ከቃጠሎው ወዲህ የሚፈለጉ መሣሪያዎችና ቁሣቁስ ሙሉ በሙሉ ለምርጫ አስፈፂሚ ባለሥልጣናቱ መድረሳቸውን ሚስተር ካቢላ ለቪኦኤ አረጋግጠዋል።

ኢቦላ ሦስት መቶ ሰው በገደለባቸው ሁለት ምሥራቃዊ ወረዳዎች ውስጥ ድምፅ የመስጫው ጊዜ ወደ ፊታችን መጋቢት እንዲተላለፍ ኮሚሽኑ መወሰኑም ትክክል ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

ምርጫው በወረዳዎቹ ውስጥ መተላለፉ ያስቆጣቸው የአካባቢው ተቃዋሚዎች ቤኒ ከተማ ውስጥ ትናንት ሁከት ማንሳታቸው ተዘግቧል።

ካቢላ ከአሥራ ሰባት ዓመታት ሥልጣን በኋላ በዚህ ምርጫ ውጤት ለሚያሸንፈው ፕሬዚዳንት እንደሚለቅቁ ተነግሯል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG