ዋሺንግተን ዲሲ —
በሀገሪቱ ከተቀሰቀሰ ትናንት ሃሙስ አንድ ዓመት የሞላው የኢቦላ ወረርሺኝ እስካሁን ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ የሚበልጡ ሰዎች ገድሏል።
በኮንጎ ሰሜን ምስራቃዊ ክፍለ ግዛት ድንበር አካባቢ ያለው ግጭት በማያሰጋ ሁኔታ ረገብ ካለ ተጨማሪ ባለሙያዎች እንልካለን ሲል ሲዲሲ አስታውቋል።
አሥራ ሁለቱ የዩናይትድ ስቴትሱ የበሽታዎች ቁጥጥር ማዕከል አባላት ከሩዋናዳ ጋር ወደምታዋስነው ዋና የመተላለፊያ ከተማ ወደጎማ ይጓዛሉ። ከተማዋ ሦስተኛ የኢቦላ ቫይረስ ታማሚ መገኘቱን ትናንት አስታውቃለች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ