በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን ጥቃት እያየለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ አሥር ሺሕ የሚሆኑ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዜጎች ባለፉት ሦስት ቀናት ድንበሯን አቋርጠው መግባታቸውን ቡሩንዲ አስታውቃለች፡፡
ወታደርቶችን ከሲቪሎች ለመለየትና በተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አማካይነት መጠለያ ለመስጠት ጥረት በመደረግ ላይ መኾኑን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።
በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በምሥራቅ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሰፊ ሥፍራዎችን የተቆጣጠሩ ሲኾን፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በደቡብ ኪቩ ግዛት ቡካቩ የተሰኘችውን ቁልፍ ከተማ ተቆጣጥረዋል። ሥፍራው ከቡሩንዲ ድንበር 50 ኪ. ሜ. ርቀት ላይ የሚገኝ መሆኑም ታውቋል።
በሺሕ የሚቆጠሩት የኮንጎ ዜጎች ወደ ቡሩንዲ የሸሹት የቡካቩ መያዝ አስደንግጧቸው እንደሆነ ታውቋል።
ቡሩንዲ ባለፈው ዓርብ ፍልሰቱን ለመግታት ስትል ለተወሰኑ ሰዓታት ድንበሯን ዘግታ እንደነበር ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
መድረክ / ፎረም