በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮንጎ ውስጥ ከአይኤስ ጋር ግንኙነት ያለው ታጣቂ ቡድን 36 ሰው ገደለ


ፎቶ ፋይል - የተቃጠሉ ቤቶች ቤኒ አቅራቢያ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ 02/18/2020
ፎቶ ፋይል - የተቃጠሉ ቤቶች ቤኒ አቅራቢያ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ 02/18/2020

ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ግዛት ውስጥ እስላማዊ መንግሥት ብሎ ራሱን ከሚጠራው ቡድን ጋር ግንኙነት ያለው ታጣቂ ቡድን ቢያንስ 36 ሰዎችን መግደሉን የሀገሪቱ የጦር ኃይል ገለጸ።

የተባበሩት ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች የተባለው ቡድን ታጣቂዎች ከሰሜን ኪቩ ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ መንደር ላይ ከረቡዕ ማታ ጀምረው ማጥቃታቸውን ከጥቃቱ በህይወት የተረፉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የተገደሉባቸውን ቤተሰቦቻቸው በመቅበር ላይ የነበሩትን የመንደሩን ነዋሪዎች ዛሬ የመንግሥቱ ባለሥልጣናት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የአካባቢው ፖለቲከኛ ኤሚል ባልኪዊሳ "በየሦስት እና አራት ቀን ሰው ያልተገደለበት ጊዜ የለም ብለው ብዛት ያለው የጦር ሰራዊት ኃይል ይምጣልን ብለን ደጋግመን የምንወተውተው በዚህ ምክንያት ነው" ብለዋል።

ምስራቅ ኮንጎ ውስጥ ላለፉት በርካታ አሰርት ከ120 በላይ ታጣቂ ቡድኖች ሲዋጉበት ቆይተዋል። የሚዋጉት ለሥልጣን እና የአካባቢውን ሀብት ለመቆጣጠር ሲሆን ማኅበረሰባቸውን ከጥቃት ለመከላከል ጥቅት ያነሱም አሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የመብት ተሟጋች ቡድኖች ኤዲኤፍ የተባለውን ታጣቂ ቡድን ሲቪሎችን ዒላማ በማድረግ ጥቃት በማድረስ ወንጅሎታል።

በቅርቡም ዩናይትድ ስቴትስ የቡድኑ መሪ ሴካ ሙሳ ባሉኩ እንዲያዝ የሚያደርግ መረጃ ለሚሰጥ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ ማስታወቁ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG