በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ የሮይተርስ ጋዜጠኛን አባረረች


ፎቶ ፋይል፦ ፈረንሳዊቱ የሮይተርስ ዘጋቢ ሶኒያ ሮሊ
ፎቶ ፋይል፦ ፈረንሳዊቱ የሮይተርስ ዘጋቢ ሶኒያ ሮሊ

ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ የሮይተርስ ጋዜጠኛን ከሀገር ማስወጣቷ ተዘገበ። ፈረንሳዊቱ የሮይተርስ ዘጋቢ ሶኒያ ሮሊ የተባረረችው የሥራ ፈቃድ ማመልከቻዋ ውድቅ ከተደረገ በኋላ መሆኑ ታውቋል።

ጋዜጠኛዋ በመስከረም ወር ያስገባችውን የሥራ ፈቃድ ማመልከቻዋን መልስ እየተጠባበቀች ባለፈው ወር ኪንሻሳ ላይ የተካሄደውን የአየር ንብረት ጉባኤ እንድትዘግብ ፈቃድ ተሰጥቷት የነበረ ሲሆን ትናንት ማክሰኞ ሀገሪቱ ኢሚግሬሽን ፖሊስ በአሮፕላን አሳፍሮ አስወጥቷታል።

የተባረረችበት ምክንያት እንዳልተገለጸላት ጋዜጠኛዋ አመልክታለች።

XS
SM
MD
LG