በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦሮሚያ አልተረጋጋችም


በቢሾፍቱ ከተማ በጥቅምት ወር በተካሄደው የኢሬቻ በዓል ላይ ከታዩት ተቃውሞዎች አንዱ።
በቢሾፍቱ ከተማ በጥቅምት ወር በተካሄደው የኢሬቻ በዓል ላይ ከታዩት ተቃውሞዎች አንዱ።

በዩኒቨርስቲዎች ትምሕርት መቋረጡንና የሰዎች ሞት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ኦሮሚያ አልተረጋጋችም
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:32 0:00

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና መደበኛ ትምሕርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት መስተጓጎሉንና ትምሕርት ቤቶች መዘጋታቸውን ተማሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዬ ገለጹ።

ተማሪዎቹ ትምሕርት ለመዘጋቱ የሚጠሰጡት ምክኒያት የተለያየ ሲሆን የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትምሕርት ሚኒስቴር በቅርቡ ካወጣው የብቃት ማረጋገጫ የመውጫ ፈተናን በመቃወም ነው።

በሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በኢትዮጵያ ሶማሌ ልዩ ፖሊስ እየተወሰደ ነው ያሉት እርምጃ እንዲቆምና መከላከያ ፖሊስ ከዩኒቨርስቲ ግቢ ይውጣ በሚል ተቃውመው ከትንናንት ጀመሮ ግቢውን ለቀው እየወጡ እነደሆነ ተናግረዋል።

በምስራቅ ሐረርጌ ጉርሱም ወረዳ ውስጥ በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በጥይት ተመቷል በሚል በተቃወሙ ወጣቶችና በመንግሥት ታጣቂዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱን ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት በዚህ ግጭት አራት ሰው ሞቷል 18 ሰዎ ቆስሏል ብሏል።

በሌላ በኩል በቄሌም ወለጋ ዞን በንቢ ዶሎ ከተማ እንዲሁ ትምሕርት ለ15 ቀናት እንደተቋረጠ ተማሪዎቹ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG