በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልሉ ግጭት የሁለቱ ኃይሎች ፍጥጫ እየተባባሰ መሆኑ ተገለጠ


ላሊበላ
ላሊበላ

ዩናይትድ ስቴትስ የህወሃት ኃይሎች ለላሊበላ ታሪካዊ ቅርሶች ጥበቃ እንዲያደርጉ ጠየቀች።

ራሱን የትግራይ ኃይል ብሎ የሚጠራው ህወሃት ላሊበላ መግባቱን እና የአማራ ክልል ኃይሎች ጥቃት እንጀምራለን ማለታቸውን ተከትሎ ግጭቱ ተባብሷል ሲል አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ዩናይትድ ስቴትስ የህወሃት ኃይሎች በታሪካዊ ቅርስነት በዩኒስኮ ለተመዘገበችው ከተማ ጥበቃ እንዲያደርጉ አሳሰበች።

ራሱን የትግራይ ሀይል ብሎ የሚጠራውና የኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪው የሕወሃት ቡድን ብሎ የሚጠራው ኃይል በአማራ ክልል በዩኔስኮ የተመዘገበ ታሪካዊ ቅርስ የሚገኝባት ላሊበላ ከተማ መግባቱን ተከትሎ የክልሉ ኃላፊዎች የአማራ ልዩ ሀይል ቅዳሜ ጥቃት እንደሚከፍት በመግለፁ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የጀመረው ግጭት በአደገኛ ሁኔታ መባባሱን አሶስዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።

የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ኃላፊ አቶ ሰማ ጥሩነህ ለክልሉ ሚዲያ የተናገሩትን ጠቅሶ አሶስዬትድ ፕሬስ እንደዘገበው «የአማራ ሕዝብ አሸባሪውን ቡድን የሚያጠፋበት ጊዜው አሁን ነው» «ሁሉም ወጥቶ እራሱን መከላከል አለበት» ሲሉ መናገራቸውን ገልጿል።

አክሎም ዘገባው በምላሹ እያንሰራራ የሚገኘውና እራሱን የትግራይ ኃይል ብሎ የሚጠራው የሕወሓት ቡድን ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ “የሞቀ አቀባበል እናደርግላቸዋለን"ሲል አውስቷል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አሸባሪው ሕወሓት ሲል የሚጠራው ቡድን በአማራና አፋር ክልል ያደረሰው ጥቃት "የመንግስትን ትዕግስት የሚፈታተን መሆኑንና ለሰብዓዊ ርዳታ ሲባል የተደረገውን የተናጠል ተኩስ ማቆም አቋሙን እንዲቀይር ሊያደርግ እንደሚችል" ማስጠንቀቁን አሶስዬትድ ፕሬስ ጨምሮ ዘግቧል።

አሶሲየትድ ፕሬስ አክሎም አቶ ጌታቸው ረዳ በስልክ በሰጡት ቃለ ምልልስ ወደ አማራ ክልል የገቡት "የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ላይ የጣለውን መንገድ መዝጋት ለማስነሳት ነው" ማለታቸውን አክሎ ጠቅሷል።

በዚህ ግጭት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሠዎች ለረሀብ አደጋ የተጋለጡ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ እና የተባበሩት መንግሥታት በዚህ ሳምንት ከፍተኛ ኃላፊዎቻቸውን በመላክ ርዳታ መግባት እንዲችል ግፊት አድርገዋል።

አቶ ጌታቸው ለአሶስዬትድ ፕሬስ ሲናገሩ «መሳሪያ ይዞ የሚተኩሰውን በሙሉ እናስቆማለን። ጥይቱን ለማስቆም አዲስ አበባ ድረስ መሄድ ካለብንም እናደርገዋለን። ግን ያን ማድረግ እንደማይኖርብን ተስፋ አደርጋለሁ።» ማለታቸውን ጠቅሷል።

በሌላ በኩል የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስን ጠቅሶ ትናንት ሮይተርስ ባወጣው ዘገባ፤ ህወሃት በዩኒስኮ ቅርስነት የተመዘገበችው ታርካዊ ከተማ ላሊበላን መቆጣጠሩን መስማታቸውን ገልፀው ለታሪካዊው ቦታ ጥበቃ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

የፈረንሳይ ቴሌቭዥን ጣቢያ የሕወሓት ቃል አቀባይ የአቶ ጌታቸውን ቃል ጠቅሶ ባጠናቀረው ዘገባ፤ ሕወሃት ዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎቹን ከላሊበላ እንዲያስወጣ ያቀረበችውን ጥሪ እንደማይቀበል ተናግረዋል።

በቅርቡ በኢትዮጵያ የስድሥት ቀናት ጉብኝት አድርገው የተመለሱት የተ መድ የሰብዐዊ ጉዳዮች ሃላፊ እና የአጣዳፊ ርዳታዎች ዋና አስተባባሪ ማርቲን ግሪፍዝ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ርዳታ ስርጭት የሚበጅ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራዩ ግጭት ያሉበት ወገኖች በሙሉ በክልሉ ያሉትን ኤርትራዊያን ስደተኞች ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለባቸው መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ራፖርተር አሳሰቡ።

የመንግሥታቱ ድርጅት የኤርትራ ሰብዐዊ መብቶች ይዞታ ልዩ ራፖርተር ዶክተር መሃመድ እብደልሳላም ባቢካር በግጭቱ መሃል ተጠምደው የሚገኙት ኤርትራዊያን ስደተኞች በሁሉም ወገኖች ዒላማ እየተደረጉ ነው ብለው በዓለም አቀፍ የሰብዐዊ መብቶች እና የሰብዐዊነት ህግ መሰረት ሁሉም ለስድተኞች ጥበቃ የመስጠት ግዴታ አለባቸው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG