የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በቀጠሉ ግጭቶችና የተፈጥሮ አደጋዎች ከ5ሽሕ የሚልቁ ትምሕር ቤቶች ተዘግተው የመማር ማስተማር ሂደቱ መቋረጡን በጥናት ማረጋገጡን አስታወቀ።
በዚህም ምክኒያት ቁጥራቸው የበዛ ሕጻናትና ሴቶች ተፈናቅለው ወደ ከተማ በመግባታቸው፣
ለጉልበት ብዝበዛ መጋለጣቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል። በተጨማሪም አዳጊዎቹ ላለዕድሜ ጋብቻ መጋለጣቸው በሪፖርቱ ላይ ጠቅሷል። ከተዘጉት በስምንት ክልሎች ከተዘጉት፣ ከ5 ሺሕ በላይ ት/ቤቶች ውስጥ ከ4ሺሕ በላይ የሚኾኑት በአማራ ክልል እንደሚገኙም በሪፖርቱ ላይ ተጠቋል። በክልሉ ባለው ግጭት ምክንያት የቀጠለው ወሲባዊና ጾታዊ ጥቃት አሳሳቢ መሆኑንም ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
መድረክ / ፎረም