በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ፍራቻን ከሰው ትከሻ ላይ ያወረደ ስብሰባ ነበር” የቪዥን ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው


የቪዥን ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው
የቪዥን ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው

ኢትዮጵያ ውስጥ እየጨመሩ የሚሄዱትን ግጭቶች ለመፍታትና የብሔራዊ አንድነት መንፈስን ለማጠናከር በሚያስችሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በቪዥን ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቭዥን(ኢሳት)አዘጋጅነት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የሁለት ቀን ውይይት ተካሂዶ ነበር። ጽዮን ግርማ ስለውይይቱና ውይይቱን በተመለከተ የቪዥን ኢትዮጵያን ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻውን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች፡፡

በከፍተኛ የትምሕርትና የሥራ ደረጃ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጥምረት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በተቋቋመው ቪዥን ኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቭዥን(ኢሳት) አዘጋጅነት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ቅዳሜና እሁድ የተካሄደው የሁለት ቀናት ውይይት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ እየጨመሩ የሚሄዱትን ግጭቶች ለመፍታትና የብሔራዊ አንድነት መንፈስን ለማጠናከር "ሽግግር፣ ዴሞክራሲና ብሔራዊ አንድነት” በሚል ውይይት ተካሂዶ ነበር፡፡

በዚህ የሁለት ቀን ስብሰባ ወደ ዐስር የሚጠጉ ምሑራን ጹሑፎቻቸውን ያቀርቡ ሲሆን የግንቦት ሰባትና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር እንዲሁም የሸንጎ ፓርቲ አመራሮች ጹሑፎቻቸውን አቅርበው ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱን የተከታተለችው ጽዮን ግርማ በውይይቱ የተነሱትን ሐሳቦችና ውይይቱን በተመለከተ የቪዥን ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻውን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

“ፍራቻን ከሰው ትከሻ ላይ ያወረደ ስብሰባ ነበር” የቪዥን ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG