በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጎንደር ላይ የጅምላ እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑ ተነግሯል


ፋሲል ግንብ
ፋሲል ግንብ

የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ “ለማስተማርና ለማሠልጠን የሚወሰዱ እርምጃዎች አሉ” ብለዋል፡፡

ጎንደር ላይ እሥራቶች እየተካሄዱ መሆኑ ተነግሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:20:37 0:00

የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ “ለማስተማርና ለማሠልጠን የሚወሰዱ እርምጃዎች አሉ” ብለዋል፡፡

በጎንደር ከተማና በአካባቢዋ ከትናንት፤ ዓርብ ከማለዳው 12 ሰዓት አንስቶ እስከ ቅዳሜ ረፋድ ድረስ ስልክና ኢንተርኔት ተቋርጦ ብዙ ሰው በአሰሣ ከየቤቱና ከየመንገዱ ተይዞ መታሠሩን አንድ የከተማዪቱ ነዋሪ ለቪኦኤ አመልክቷል፡፡

ከዚያ በተጨማሪም የወልቃት የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላትና ደጋፊዎቻቸውንም የማሳደድ ተግባር እየተካሄደ መሆኑን እንደሚያውቅ ነዋሪው ገልጿል፡፡

እንዲሁም የሌለ የብሄሮችን ቅራኔና ግጭት ለመፍጠርም እየተጣረ መሆኑን ነዋሪው ተናግሯል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሰሞኑን ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አንስቶ በአንዳንድ አካባቢዎች መብራት እንደሚጠፋና ይህም ሆን ተብሎ ሰዉ ሚዛናዊ መረጃ ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እንዳያገኝ የታሰበ ነው ብሎ እንደሚጠረጥር ገልጿል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በበኩላቸው አለ ስለሚባለው እሥራት ተጠይቀው “የተሣሣቱ ወጣቶችን ለማስተማርና ሥልጠና ለመሥጠት ሲባል” እየተያዙ ወደ ተዘጋጀ ቦታ እንደሚወሰዱ እንደሚደረግ ገልፀው መንግሥት ግን “የማሠርና የማንገላታት ፍላጎት” የለውም ብለዋል፡፡

አቶ ንጉሡ በክልሉ ውስጥ በአመዛኙ ሠላም መመለሱንና ባለፈው ዓመት ውስጥ ስለጠፋው ሕይወት እርሣቸውም መንግሥታቸውም እንደሚያዝኑ ገልፀው “አዲሱ ዓመት ችግሮች በውይይት የሚፈቱበትና የሰላም እንዲሆን እመኛለሁ” ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG