ዋሺንግተን ዲሲ —
ጣልያን አገር ውስጥ ከሚላን ከተማ ወጣ ብሎ አንድ ባቡር ተገልብጦ ሦስት ሰዎች ሞተው ሌሎች አሥር በጠና መቁሰላቸው ታወቀ።
አደጋው ዛሬ ሐሙስ የደረሰው፣ ከሴርሞና ከተማ ወደ ሚላን ያመራ በነበረው የመንገደኞች ባቡር ላይ ሲሆን፣ ሰገሬት ከተማ ሲቃረብ ነው የመካከለኞቹ ፉርጎዎች ከሀዲዱ ሊወጡና ሊገለበጥ የቻለው።
የአደጋ መከላከልና አስወጋጅ ቡድን ወደ ስፍራው በመሄድ ለቆሰሉት መንገደኞች እርዳታ ማድረጉም ታውቋል። በአደጋው የተነሳም የአካባቢው የባቡር አገልግሎት ተቋርጦ ውሏል።
እአአ በ2016 ደቡባዊ ጣልያን ውስጥ በደረሰ የባቡር አደጋ 23 ሰዎች መሞታቸው አይረሳም።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ