በየመን ጠረፍ አቅራቢያ ሲያልፍ የነበረ የነዳጅ እና የሌላም ፈሳሽ ጭነት ማጓጋዣ መርከብ ዛሬ ሰኞ ጥቃት እንደደረሰበት ተገለጠ፡፡
ሁለት የደሕንነት ድርጅቶች እንዳሉት ከሆነ ጥቃቱ የተሰነዘረበት ከትናንሽ ጀልባዎች ሲሆን ሆኖም በመርከቡ ላይም ሆነ በሠራተኞቹ ላይ ደርሷል የተባለ ጉዳት የለም፡፡ መርከቡም በደህና የታቀደለት ቦታ ደርሷል፡፡
ጥቃቱ የተፈጸመው በኢራን የሚታገዙት ሁቲ አማጽያን ከሚቆጣጠሯት ከሆዴይዳ ወደብ ከተማ ሰባ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የባሕር ክልል ላይ መሆኑን የእንግሊዝ የማሪታይም ንግድ እንቅስቃሴ ተቋም አመልክቷል፡፡
ጋዛ ላይ በሚካሄደው ጦርነት ለፍልስጥኤማዊያን ድጋፋችንን ለመግለጽ ነው ያሉት የየመን ሁቲ ታጣቂዎች እ አ አ ከሕዳር ወር ጀምሮ በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ መርከቦች ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ ከርመዋል፡፡
መድረክ / ፎረም