በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአየር ኃይሉ ኮሎኔል ጋዲሳ ጉማ አረፉ


ኮሎኔል ጋዲሳ ጉማ
ኮሎኔል ጋዲሳ ጉማ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የመጀመሪያ ካዴቶችና አብራሪዎች አንዱ የነበሩት ኮሎኔል ጋዲሳ ጉማ በዘጠና ሰባት ዓመት ዕድሜአቸው ዛሬ አረፉ።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የመጀመሪያ ካዴቶችና አብራሪዎች አንዱ የነበሩት ኮሎኔል ጋዲሳ ጉማ በዘጠና ሰባት ዓመት ዕድሜአቸው ዛሬ አረፉ።

ለኮሎኔል ጋዲሳ የፊታችን ቅዳሜ፣ ጥቅምት 25/2010 ዓ.ም ወይም ኖቬምበር 4/2017 ከረፋዱ 5 ስዓት /11AM/ በኦክላንድ መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ፀሎተ ፍትሃት ተከናውኖ ከቀኑ 7 ሰዓት /1PM/ አስከሬናቸው በሎንትሪ መካነ መቃብር እንደሚያርፍ ታውቋል፡፡

ኮሎኔል ጋዲሳ የተወለዱት በወለጋ ጠቅላይ ግዛት ቡሪ ሲሆን ገና በሕፃንነታቸው አይሮፕላን የማብረር ፍቅርና ሕልም እንደነበራቸው በቅርቡ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ገልፀው በኋላ ግን እርሣቸው ባልጠበቁት ሁኔታ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ፊት ቀርበው የአየር ኃይል ወታደርና አብራሪ ሆነው እንዲሠለጥኑ እንደተፈቀደላቸው ተናግረዋል።

ኮሎኔል ጋዲሳ ጉማ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለድፍን ጥቁር አፍሪካም ከመጀመሪያዎቹ የአየር ኃይል ባለደረቦች አንዱ ነበሩ። ኮሎኔል ጋዲሳ ጉማ ያረፉት ኦክላንድ-ካሊፎርኒያ በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው፣ ዘመዶቻቸውና ውዳጆቻቸው በተገኙበት በክብር መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ስቪኦኤ ገልፀዋል።

ኮሎኔል ጋዲሳ በቅርቡ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ የተመረኮዞ የቪዲዮ ዘገባ ከሰሞኑ እናቀርብላችኋለን፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG