በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንክን ቻይና የሩሲያን መከላከያ ለማሳደግ ስለምታደርገው ድጋፍ አስጠነቀቁ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ከቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ቤጂንግ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ከቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ቤጂንግ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ዛሬ ዐርብ እንደተናገሩት፣ ቻይና ለሩሲያ የመከላከያ ኢንዱስትሪ በምታደርገው ድጋፍ ላይ “ከባድ ስጋት” እንዳላቸው ገልጸው፣ ዋሽንግተን በጉዳዩ ላይ ማዕቀብ ልትጥል እንደምትችል የቻይና መሪዎችን አስጠንቅቀዋል።

የብሊንክን ማስጠንቀቂያ የተሰማው፣ ከቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እና ከሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ መሪዎች ጋራ በሁለቱ ኀይሎች መካከል ባሉ ሰፊ አለመግባባቶች ላይ ቤጂንግ ውስጥ በተወያዩበት ወቅት ነው።

ከብሊክን ዋና የንግግር አንጀንዳዎች መካከል፣ “ሩስያ በዩክሬን ላይ በምታካሒደው ጦርነት ጥቅም ላይ የሚውሉ መሣሪያዎችን ለመፍጠር የምትጠቀምባቸውን እንደ ማይክሮ ቺፕ፣ የማሽን መሣሪያዎች እና ሌሎች የቻይና አቅርቦቶች ይገኙበታል፤” ሲሉ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

ከፕሬዚዳንት ሺ ጋራ ከተወያዩ በኋላ ብሊንክን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ “የሩስያን የኢንዱስትሪ መሠረት ማሳደግ፣ የመላ አውሮፓን ደኅንነትም እንደሚያሰጋ” ለቻይናው መሪ ነግረዋቸዋል፡፡

ለቻይና ስናንገር እንደቆየነው፣ ከአትላንቲክ ማዶ ያለውን ደኅንነት ማረጋገጥ የአሜሪካ ዋና ፍላጎት ነው፤”

“ቤጂንግ፣ ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቂያ በኋላ ለአውሮፓ ደኅንነት ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥረውን ድርጊት እየደገፈች ከአውሮፓ ጋራ የተሻለ ግንኙነት መፍጠር አትችልም፤” ያሉት ብሊንክን አክለው፣ “ዛሬ(ዐርብ) ባደረግነው ውይይት ግልጽ እንዳደረግኹት፣ ቻይና ይህን ችግር የማትፈታ ከኾነ እኛ እንፈታዋለን!” ብለዋል፡፡

“ለቻይና ስናንገር እንደቆየነው፣ ከአትላንቲክ ማዶ ያለውን ደኅንነት ማረጋገጥ የአሜሪካ ዋና ፍላጎት ነው፤” ብለዋል ብሊንክን፡፡

የዩናትይድ ስቴትስ ባለሥልጣናት፣ ቻይና ለወታደራዊም ኾነ ሲቪል አገልግሎቶች ጥምር ጥቅም የሚውሉ ዕቃዎችን ለሩሲያ እንዳታቀርብ ተጨማሪ ማዕቀብ እንደሚጣል፣ ለሳምንታት ፍንጭ ሲሰጡ ሰንብተዋል፡፡

ዋሽንግተን ይህን ርምጃዋን ምን ያህል እንደምትገፋበት ግልጽ አይደለም፡፡ ይኹን እንጂ፣ ዋና ዋና የቻይና ባንኮችን ከአሜሪካ የፋይናንስ ሥርዓት ማቋረጡም፣ የአሜሪካንና የዓለምን ኢኮኖሚ በአጠቃላይ ሊጎዳ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

ብሊንክን፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከ100 በሚበልጡ የቻይና አካላት ላይ ማዕቀብ እንደጣለች ቢያስታውቁም፣ በዛሬ ዐርብ መግለጫቸው ላይ ግን፣ ወደፊት ሊወሰዱ ስለሚችሉ ርምጃዎች ዝርዝር አልተናገሩም።

ቻይና፣ ከዋና የንግድ አጋርዋ ሩስያ ጋራ፣ በመደበኛ የኢኮኖሚ ልውውጥ ላይ ብቻ እንደምትሠራ በመግለጽ፣ የብሊንክንን ስጋት ተቃውማለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG