በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሲኤንኤን የትረምፕ አስተዳደርን በፍ/ቤት ከሰሰ


የዩናይትድ ስቴትሱ የቴሌቭዢን ዜና አውታር /ሲኤንኤን/ የትረምፕ አስተዳደርን በፍርድ ቤት ከሰሰ።

የዩናይትድ ስቴትሱ የቴሌቭዢን ዜና አውታር /ሲኤንኤን/ የትረምፕ አስተዳደርን በፍርድ ቤት ከሰሰ።

ሲኤንኤን ክሱን የምሰረተው ባለፈው ሳምንት የፕሬስ ፈቃዱን በዋይት ኃውስ የተነጠቀው ሪፖርተሩ ጂም አኮስታ ፈቃዱ ተመልሶለት ሥራውን እንዲቀጥል በመጠየቅ ነው። የትረምፕ አስተዳደር ያለአግባብ የጋዜጠኛውን ፈቃድ መሰረዙ ሲኤንኤንና ጂም አኮስታ በሕገ መንግሥቱ የመጀመሪያ ማሻሻያ የሚፈቅደውን የፕሬስ ነፃነታቸውን እና በአምስተኛው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ የተደነገገውን የሕጋዊ ሂደት መብት የጣሰ አድራጎት እንደሆነ አመልክቷል።

ፍርድ ቤቱ በአስቸኳይ የጂም አኮስታ የፕሬስ ፈቃድ እንዲመለስለት እና ከእንግዲህም እንዲህ ያለ ተግባር እንዳይፈፀምበት ጠይቀናል ብሉዋል ሲኤንኤን፡፡

ከሲኤንኤን ስመጥር ጋዜጠኞች አንዱ የሆነው ጂም አኮስታ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕንና ሌሎቹንም ከፍተኛ የዋይት ኃውስ ባለሥልጣናት በጠንካራ ጥያቄዎች በማፋጠጥ ይታወቃል።

የትረምፕ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት የዋይት ኃውስ ሪፖርተርነት ፈቃዱን የቀማው ፕሬዚደንቱ ከማዕከላዊ አሜሪካ በብዛት ወደዩንይትድ ስቴትስ ለመግባት እየጎረፉ ያሉትን ፍልሰተኞች “ወረራ” ብለው መጥራታቸውን አስመልክቶ በሞጋች ጥያቄ ውጥር ካደረጋቸው በኋላ መሆኑ ይታወሳል። በዚሁ መሃል ጋዜጠኛው ከእጁ ላይ ማይክሮፎኑን ልትነጥቀው የሞከረችውን የዋይት ኃውስ የፕሬስ ክፍል ረዳት እጁን አሳርፎባታል ብለው የቤተ መንግሥቱ ባለሥልጣናት ወንጅለውታል። በወቅቱ የተቀረፀው የቪዲዮ ምስል ግን ጂም አኮስታ የተባለቸው ሰራተኛ ላይ ጉልበት ፈጽሞ አልተጠቀመም።

የዋይት ኃውስ ዘጋቢዎች ማኅበር ፕሬዚደንት እዕሊቪዬ ኖክስ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ስራቸውን በተመለከተ የሚዘግቡ ጋዜጠኞችን ራሳቸው በዘፈቀደ መምረጥ ውስጥ መግባት የለባቸውም ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG