በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለምቀፍ ደረጃ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው


በዓለምቀፍ ደረጃ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ተቃውሞ የሚካሄድበት ዕለት ተጀምሯል። አስተባባሪዎቹ ከአንድ ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች እንደሚሳተፉበት ይጠብቃሉ።

የዓለም የአየር ንብረት ከሚገባው በላይ እንዲሞቅ ምክንያት የሆኑትን ሰው ሰራሽ ችግሮችን በመቃወም የሚደረግ ከዚህ ቀደም ያልታየ ብዛት ያለው ሰልፍ እንደሚሆን ተገልጿል።

የዛሬው ሰልፍ የተጀመረው በእስያ ዙርያ ሲሆን በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችና ሌሎችም ተሳትፈውበታል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስለጉዳዩ ለመነጋገር ጉባዔ ከመጀምሩ በፊት በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ለማደረግ ነው ሰልፎች የሚካሄዱት።

አውስትራሊያ ላይ ብቻ በአንዳንድ የአከባቢ ባለሥልጣኖች፣ በትምህርት ቤቶችና በንግድ ተቋማት የተደገፉ 300,000 የሚሆኑ ልጆችና ጎልማሶች ተሰልፈዋል። በሀገሪቱ ታሪክ የተደረገ ትልቁ የአየር ሙቀት ተቃውሞ ነው ተብሏል።

በዩናይትድ ስቴትስም ሰልፎች እየተካሄዱ ነው። አስተባባሪዎች እንደሚሉት ከ800 በላይ ሰልፎች እንዲካሄዱ ታቅዷል።

አፍሪካ ውስጥ ደግሞ በናይሮቢ ኬንያ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ከተሞች ጆሀንስበርጋና ፕሪቶርያ ፀረ የአየር ንብረት ሙቀት ሰልፎች ተካሂደዋል። አፍሪካ ከሁሉም በላይ የአየር ለውጥ ለሚያስከትለው ችግር የተጋለጠች መሆኗን የመከላከል አቅሟ ዝቅተኛ መሆኑ ተገልጿል። በሌሎች በርካታ ሀገሮችም ሰልፎች ተካሂደዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG