በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአየር ንብረት ለውጥ አክቲቪስቶች


የአየር ንብረት ለውጥ አክቲቪስቶች የለንደኑ ሂትሮ አውሮፕላን ማረፍያ በረራዎችን ለማሰናከል ሲሉ በአቅራቢያው ሰው አልባ አውሮፕላኖችን/ድሮኖችን/ የማብረር ዕቅድ ቢኖራቸውም ዓለምቅፉ የአውሮፕላን ማረፍያ ዛሬ ክፍት ሆኖ ውሏል።

አክቲቪስቶቹ ከሂትሮ አውሮፕላን ማረፍያ በአምስት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ድሮኖችን ለማብረር ማቀዳቸው ሲገለፅ ዓላማቸውም የብሪታንያ መንግሥት የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ በርትቶ እንዲሰራ ግፊት ለማድረግ ነው።

ይሁንና የድሮን በረራው ተሰናክሎ አውሮፕላን ማረፍያው መደበኛ ሥራውን እንደቀጠለ ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የአክቲቪስቶቹ ቡድን በገለፀው መሰረት አውሮፕላን ማረፍያው የመጀመርያዎችን የድሮን በረራን ለማሰናከል የበረራ መስመር ምልክቶችን የማፈን ዕርምጃ ወሰደ።

በአውሮፕላን ማረፍያው ላይ ከተሞከረው የተቃውሞ ተግባር ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች ዛሬ ተይዘዋል፣ ትናንት አምስት ታስረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG