በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ችግር በማነሳሳት የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ናቸው


ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ

ሰሞኑን በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተከሰተውን ችግር በማነሳሳት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በተማሪዎች ጥቆማ በቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠቅሶ ለመንግሥት ቅርበት ያልው ፋና ዘገበ።

ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሽት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ተማሪዎች መካከል የተፈጠረ የግል ፀብ ወደ ቡድን ግጭት አምርቶ የሁለት ተማሪዎች ህይወት መጥፋቱና የተወሰኑ ተማሪዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።

በተከታዮቹ ቀናትም መሰል ግጭቶች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መከሰታቸውን የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል ይላል ዘገባው።

ከወልድያ ባሻገር መቱ፣ ጅማ እና መዳወላቡ ዩኒቨርሲቲዎች ችግር የተከሰተባቸው ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን፣ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው ችግሩን በማነሳሳት የተጠረጠሩ ሰዎችም ከትናንት ምሽት ጀምሮ በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው ማለታቸው በፋና ዘገባ ተጠቅሶአል።

ተማሪዎቹ ስጋት ስለገባቸው ከግቢ እየለቀቁ መውጣታቸውን ጠቅሰው፥ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ወደ ግቢያቸው እንዲመለሱ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

መንግሥት ከሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዳይቋረጥ ተማሪዎች ተረጋግተው እንዲማሩ እና ከተጠለሉባቸው የዕምነት ተቋማት እንዲመለሱ እያደረገና እያወያያ መሆኑንም አስረድቷል።

ወላጆች የሚዲያ ስራተኞች ፣ የየአካባቢው ነዋሪዎች ተማሪዎቹን እንዲያረጋጉም ጠይቀዋል።

የተማሪዎችን መታወቂያ በመቀማትና ወደ ጊቢ በመግባት ችግሩን ይፍጥራሉ ያሉዋቸዉ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ሚኒስትሩ ማሳሰባቸው ተዘግቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG