በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሱዳን ዳርፉር ውስጥ በተካሄደ ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች ተገደሉ


በሱዳን ዳርፉር ክፍለ ግዛት በአረቦች እና አረብ ባልሆኑ ቡድኖች መካከል በተካሂደ ግጭት ከአንድ መቶ የሚበልጡ ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። በክፍለ ግዛቲቱ በቅርብ ወራት በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል።

ይህ የኋለኛው ግጭት ባለፈው ሳምንት የተቀሰቀሰው ከምዕራብ ዳርፉር ዋና ከተማ ከኤል ጌኔይና 160 ኪሎ ሜትር በሚገኘው በኮልቡስ ወረዳ በሪዜይጋት አረቦች እና አረብ ባልሆኑት ጊሚር ጎሳዎች መካከል መሆኑ ተዘግቧል።

ይህ የኋለኛው ብጥብጥ የሚያሳየው በጂኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን የተመራው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በዳርፉር የጸጥታው ሁኔታ ይበልጡን መደፍረሱን የሚያመለክት መሆኑ ተገልጿል።

ትናንት ሰኞ የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ተወካይ ቮልከር ፐርዝ ኮልቡስ ላይ የተካሄደው ብጥብጥ ተቀባይነት እንደሊለው ገልጸው የግጭቱ መሰረታዊ መንስዔ መፍትሄ እንደሚያስፈልገው አጉልቶ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG