በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኻርቱም ውስጥ 37 ሰዎች መገደላቸውን አምነስቲ አስታወቀ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም ውስጥ የፀጥታ ኃይሎች 37 ሰዎች መግደላቸውን የሚጠቁም መረጃ እንደደረሰው አምነስቲ አስታወቀ።

ሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም ውስጥ የፀጥታ ኃይሎች 37 ሰዎች መግደላቸውን የሚጠቁም መረጃ እንደደረሰው አምነስቲ አስታወቀ።

የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል-ባሺር ሥልጣን እንዲለቅቁ የሚጠይቁ ተቃዋሚዎች በቤተመንግሥቱ አካባቢ ዛሬ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ካሳወቁ በኋላ በኻርቱም ጎዳናዎች ላይ ሰልፍ በታኝ ፖሊስና ወታደሮች ተሠማርተው ውለዋል።

በሺኾች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በዋና ከተማዪቱ መንገዶች ላይ ከታጠቁ የፀጥታ ኃይሎች ጋር መፋጠጣቸውን የሚያሳዩ የቪድዮ ምስሎች ትዊተር ላይ ተለቅቀዋል።

ለአንድ ሣምንት የዘለቁት ተቃውሞዎች የተቀሰቀሱት ሱዳን ውስጥ በርትቶ ይታያል በተባለው የምግብና የነዳጅ እጥረት፣ እንዲሁም የዳቦ ዋጋ በማሻቀቡ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

ዜጎች “የተሻለ ሕይወት እንዲኖራቸው ያስችላሉ” ያሏቸውን የምጣኔኃብት ማሻሻያዎች እንደሚያደርጉ ፕሬዚዳንት አል-ባሺር ትናንት ቃል ገብተው ነበር።

የመብቶች ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው መግለጫ 37 ሰዎች ከተሠማሩት የፀጥታ ኃይሎች በተከፈቱ ተኩሶች መገደላቸውን የሚጠቁም መረጃ “የማምነው” ካለው ምንጭ እንደደረሰው አመልክቷል።

የአምነስቲ የምሥራቅ አፍሪካ የታላላቅ ኃይቆችና የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ምክትል ዳይሬክተር ሳራ ጃክሰን በሰጡት ቃል “የታጠቁት የመንግሥት ኃይሎች ባልታጠቁ ሰልፈኞች ላይ ገዳይ የሆነ መደዳ ተኩስ ከፍተዋል” ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ፣ የእንግሊዝ፣ የኖርዌይና የካናዳ መንግሥታት ትናንት በጋራ ባወጡት መግለጫ የሱዳን የፀጥታ ኃይሎች በተቃዋሚዎቹ ላይ ቀጥተኛ ተኩስ የመክፈታቸው ነገር እንደሚያሳስባቸው አስታውቀዋል።

ተቃውሞዎቹ የተነሱት በሠርጎ-ገቦችና በአሻጥረኞች ነው ሲል የሱዳን መንግሥት ክሥ አሰምቷል።

የሰባ አምስት ዓመቱ አል-ባሽር ሥልጣን በመፈንቅለ-መንግሥት ከያዙ አንስቶ ላለፉት ሃያ ዘጠኝ ዓመታት እየመሩ ይገኛሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG