በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡርኪና ፋሶ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የፈንጂ አደጋ 35 ሰዎች ተገደሉ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ቡርኪና ፋሶ ሰሜናዊ ግዛት ውስጥ ትናንት ሰኞ በተቀበረ ፈንጂ ላይ በወጣ ተሽከርካሪ በደረሰ ፍንዳታ 35 ሰዎች ሲሞቱ 37 ደግሞ መቁሰላቸውን የአገሪቱ ጊዚያዊ መንግሥት አስታወቀ፡፡

ተሽከርካሪው ወደ ኦጋዱጉ በአጀብ ያመሩ ከነበሩ ተሽከርካሪዎች መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፈንጂ አደጋው የደረሰው የእስላማዊ ታጣቂዎች ጥቃት እያየለ በመጣበት ዲጅቦ እና ቡዋሩዛኛ በተባሉ ከተሞች መካከል በሚገኝ ስፍራ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ባላፉት አስር ዓመታት በምዕራብ አፍሪካ ከአልቃይዳና እስላማዊ መንግሥት ጋር በተሳሰሩ ቡድኖች የሚደርሰው ጥቃት እያየለ መምጣቱን የሮይተርስ ዘገባ ጨምሮ አመልክቷል፡፡

በቡርኪናፋሶ ከአስር ሰዎች አንዱ በግጭትና በምግብ ዋስትና እጦት የተነሳ አካባቢውን ለቆ የተፈናቀለ መሆኑ በዘገባው ተግለጿል፡፡

የቡርኪናፋሶው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ራች ካቦሬ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተወገዱበት ከባላፈው ጥር ወዲህ በአገሪቱ ተስፋ መቁረጥ መንገሱ ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG