በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮንጎ ውስጥ 46 ሲቪሎች ተገደሉ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ኮንጎ ዴምክራሲያዊት ሪፖብሊክ ምሥራቃዊ አካባቢዎች ውስጥ እሥላማዊ ታጣቂዎች ትናንት ፈፀሙት በተባለ ጥቃት 46 ሲቪሎች መገደላቸውን የክፍለሃገሩ የደህንነት ኃላፊ አድጆ ጊዲ ለሮይተርስ ገልፀዋል።

የተባበሩት ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የሚባል ቡድን ከጥቃቱ ጀርባ እንዳለ በመጠቆም የከሰሱት ጊዲ ኢሩሙ በሚባለው አካባቢ ወደምትገኘው ቀበሌ ወታደሮች መላካቸውንና ምርመራ መጀመሩን አመልክተዋል። ምሥራቃዊዎቹ የኮንጎ አካባቢዎች ላይ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በዚሁ ታጣቂ ቡድን በተጣሉ ጥቂቶች ከአንድ ሺህ በላይ ሲቪሎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ይጠቁማል።

በዩሃንዳ፣ በሩዋንዳና በቡሩንዲ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ከመቶ በላይ ታጣቂ ቡድኖች በየጫካው እንደሚገኙ ተዘግቧል። ቀደም ሲል ለተጣሉት ጥቃቶች እሥላማዊ መንግሥት ቡድን ኃላፊነት ቢወስድም የመንግሥታቱ ድርጅት ግን በታጣቂዎቹና በእሥላማዊ መንግሥት ቡድን መካከል ግንኙነት ሰለመኖሩ ማረጋገጫ አለማግኘቱን ይናገራል።

XS
SM
MD
LG