በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጀሲ ጃክሰንና ባለቤታቸው ሆስፒታል ገቡ


ፎቶ ፋይል፦የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ጀሲ ጃክሰን
ፎቶ ፋይል፦የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ጀሲ ጃክሰን

የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ጀሲ ጃክሰን እና ባለቤታቸው ለኮቪድ 19 ቫይረስ ተጋላጭ በመሆናቸው ሆስፒታል መግባታቸው ወንድ ልጃቸው ትናንት እሁድ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ለ79 ዓመቱ ጃክሰንን እና ለ77 ዓመቷ ባለቤታቸው ጃኩሊን፣ ባላቸው እድሜ የተነሳ ለጥንቃቄው አስፈላጊውን ምርመራ ሁሉ እያደረግንላቸው ሲሉ፣ ቺካጎ በሚገኘው የኖርዝ ዌስት ዩኒቨርስቲ ሜሞሪያል ሆስፒታል የሚገኙ ሀኪሞች አስታውቀዋል፡፡

እኤአ በ2017 የፓርኪንሰንስ በሽታ ህክምና የተደረገላቸው ጄሲ ጃክሰን እኤአ ከ1960ዎቹ አጋማሽ ጀምረው እኤአ 1968 ከተገደሉት ከነማርቲን ሉተር ኪንግ ጋር የሰብአዊ መብት ትግል እንቅስቃሴን የተሳተፉና የመሩ ናቸው፡፡

በ1980ዎቹም ለሁለት ጊዜ ያህል የዴሞክራቲክ ፕሬዚዳንት እጩ በመሆን መወዳደራቸው ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG