በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጂና ሃስፐል በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ፊት ቀርበው ለጥያቄዎች መልስ ሰጡ

CIA nominee Gina Haspel is seated for a confirmation hearing of the Senate Intelligence Committee on Capitol Hill, May 9, 2018 in Washington.
CIA nominee Gina Haspel is seated for a confirmation hearing of the Senate Intelligence Committee on Capitol Hill, May 9, 2018 in Washington.

ነባር የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ የሥለላ አገልግሎት /ሲአይኤ/ ሰራተኛና የወቅቱ የአገልግሎቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ጂና ሃስፐል ዛሬ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ፊት ቀርበው ለጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል። ከዚህ ቀደም በአገልግሎቱ አሰራር የነበረውን ጭካኔ የታከለበት የምርመራ ዘዴን ለማቆም ለምክር ቤት አባላቱ ቃል ገብተዋል።

ሃስፐል የሥለላ መሥርያ ቤት ኃላፊ እንዲሆኑ በፕሬዚዳንት ትረምፕ የተሰያሙ ሲሆን የምክር ቤት አባላት ፊት የቀረቡት ሹመታቸውን ለማፅደቅ ወይም ላለማፅደቅ ለመወሰን ነው።

“ግልፅ በሆነና በማያወላዳ መንገድ ቃል ልገባላችሁ እችላለሁ። ሲአይኤ በኔ አመራር ሥር እንዲህ ዓይነቱ የማሰርና የምርመራ ፕሮግራም እንዲቀጥል አያደርግም” ሲሉ ለምክር ቤት አባላቱ ቃል ገብተዋል።

ሃስፐል በዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወኛ ምክር ቤት የሥላለ ኮሚቴ ፊት በቀረቡበት ወቅት የገጠምዋቸው ጥያቂዎች አገልግሎቱ በሚፈፅመው አስክፊ የምርመራ ዘዴ ላይ በነበራቸው ሚናና ተግባሩ እንዳይታወቅ ሲሉ ለመሸፋፈን ሳይሞክሩ አልቀርም በሚሉት ላይ ያተኮረ ነበር።

ሃስፐል ከ16 ዓመታት በፊት ታይላንድ የነበረውን ሚስጢራዊ የ/ሲአይኤ/ እሥር ቤትን ይቆጣጠሩ በነበሩበት ወቅት በእስረኞች ላይ ይፈፀም የነበረው አስከፊ የምርመራ ዘዴ ሰቆቃ ነው በሚል ሲወገዝ ቆይቷል።

ዘጠና ሁለት ስለ ምርመራው ዘዴ የሚያሳዩ የቪድዮ ምስሎች እንዲደመሰሱ መመርያ አስተላልፈዋል በሚልም ሃስፐል ተከሰዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG