ዌብ ሣይቶቹ ያካባቢውን ቤተ ክርስቲያን አባላት ጠቅሰው ጥቃቱን በመፍራት አራት ሺህ ክርስቲያኖች ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሸሻቸውን፥ በትንሹ አንድ ሰው ደግሞ አሰንዳቦ ከተማ አጠገብ ተገድሏል ማለታቸውን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሺመልስ ከማል ድንገቱን አስመልክቶ ያላቸው ዝርዝር በጣም ውሱን ነው። ባለሥልጣኑ ከቪኦኤ ጋር በቴሌፎን ባደረጉት ቃለ ምልልስ ግን፥ ፖሊስ በርካታ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ማሠሩን ተናግረዋል።
አቶ ሺመልስ በዚህ የቴሌፎን መግለጫቸው፥ ምን ያህል ተጠርጣሪዎች ተይዘው እንደታሠሩ፥ ወይም ስለቀረበባቸው ክስ ምንነት በዝርዝር አልገለፁም።
የክርስቲያን ዌብ ሣይቶቹ ሪፖርት ግን ቤተ-ፀሎቶቹን በማቃጠሉ ተግባር በሺሆች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተባብረዋል ይላሉ።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ -