በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንጋፋው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቅ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሃንስ አርፉ።


Ethiopia Church Ceremony
Ethiopia Church Ceremony

መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሃንስ ያረፉት ባለፈው ቅዳሜ ሲሆን፣ በስሜን አሜሪካ ከሚገኘው ሲኖዶስ ጋር የተካሄደ የስላምና አንድነት ጉባኤ ተካፍለው ሲመለሱ ነው።

: በስሜን አሜሪካ ከሚገኘው ሲኖዶስ ጋር የተካሄደ የስላምና አንድነት ጉባኤ የተመለሱት:አንጋፋው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቅ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሃንስ ባላፈው ቅዳሜ አዲስ አበባ እንደገቡ አርፈዋል።

በደርግ ዘመን ፓትርያርክ ሆነው ባገለገሉት አቡነ መርቆርዮስ የሚመራንና እራሱን ህጋዊ የኢትዮጵያው ኦርትቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ብሎ በሚጠራው በሰሜን አሜሪካ የሚገኝ ሲሆን፣ ሌላው በብጹእ ወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የሚመራዉ የኢትዮጵያው ኦርትቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ደግሞ ይህንን አይቀበልም። የሃስት ሲኖዶስን አቋቁሜአለሁ በማለት ምእመናንን ሲያጭበርብር ቆይቷል በማለት ጥር 25 1999 ባወጣው መግለጫ አቡነ መርቆርዮስ ላይ ቃለ ውግዝት አስተላልፏል፣ የማእረግ ስማቸው መነሳቱን በዚሁ መግለጫው ጠቅሶአል። በአቡነ መርቆርዮስ የሚመራውም ሌላው ቡድን በአቡነ ጳውሎስ ላይ ወዲያው ውግዘት አስተላልፎአል።

ሁለቱን ወገኖች ለማቀራረብና አንድነት ለመፍጠር በዋሽንግተን የተመሰርተው የኢትዮጵያ ኦርትቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአንድነት ጉባኤ ላይ አራት አባላት ያሉበት ልኡካን ተግኝቶ ነበር። ቡድኑ ባላፈው ቅዳሜ ወደ አዲስ አበባ የተመለስ ሲሆን፣ ከአባላቱ አንዱ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሃንስ በድንገት አርፈዋል። እስካሁን ስለ ውይይቱ የውጣ መግለጫ የለም።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቅ መምህራን ካሳሁን ሙጬ ለዘጋቢያችን እስክንድር ፍሬው የሰጡትን ቃል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG