በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዛሬ ገና ነው፤ ገና በአሜሪካ


ኢየሱስ ተወለደ
ኢየሱስ ተወለደ

ዛሬ ገና ነው፤ ለኢትዮጵያና ለጥንታዊ የኦርቶዶክስና ኮፕቲክ ክርስትና ጊዜው ገና ቢሆንም ለገሚስ ዓለም ዛሬ ገና ነው፡፡




በሽብርቅርቅ የተሸለመች የገና ዛፍ
በሽብርቅርቅ የተሸለመች የገና ዛፍ

please wait

No media source currently available

0:00 0:38:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዛሬ ገና ነው፤ ለኢትዮጵያና ለጥንታዊ የኦርቶዶክስና ኮፕቲክ ክርስትና ጊዜው ገና ቢሆንም ለገሚስ ዓለም ዛሬ ገና ነው፡፡

ለዛሬው ገና ታዲያ የአሜሪካና የሌሎችም ሃገሮች የጥበብ ሰዎች ለበዓል ለማድረስ ደፋ ቀና ሲሉ የሰነበቱባቸውን የፈጠራ ውጤቶቻቸውን፣ ዝማሬዎቻቸውን አበርክተዋል፡፡
ሩዶልፍ፤ አፍንጫው የቀላው አጋዘን የገና አባት የገና ሥጦታዎችን ጭነው ይጋሉቡታል
ሩዶልፍ፤ አፍንጫው የቀላው አጋዘን የገና አባት የገና ሥጦታዎችን ጭነው ይጋሉቡታል

በሌላ በኩል ደግሞ የብዙ የዓለም ሕዝቦች ሃገር በሆነችው አሜሪካ ገና እንደየገፅታው ይከበራል፡፡

የ “ክለብ ሃያ ሰባት መረዳጃ ዕድር” አባላት ኢትዮጵያዊያን የዛሬውን የገና በዐል ሲያከብሩ ከ15 ዓመት በላይ ሆኗቸዋል። ፀሐፊውን አቶ አበባየሁ አሉላንና መሥራቹን አቶ አቤል ሣህሌን በኢትዮጵያዊያን በአሜሪካ ልዩ ዝግጅት አነጋግረናቸዋል፡፡

«ክለብ ሃያ-ሰባት እንባላለን፤ ከተሰባሰብን ከ15 ዓመት በላይ ሆኖናል፤ በያመቱ እንደምናደርገው ዘንድሮም የChristmas ዕለት እንሰበሰባለን፤ መሰባሰባችንና አንድነታችን ለሌላው ኢትዮጵያዊ ልምድ ያካፍላል ብለን እናምናለንና ብቅ ብላችሁ ብታዩን» በማለት ስለጠሩን አዲሱ አበበ ብቅ ብሎ አይቷቸዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን በአሜሪካም እንኳን ለአውሮፓዊያኑ የገና በዐል አደረሳችሁ ይላል።

የተያያዘው የድምፅ ፋይል በአሜሪካ የተለያዩ ሕዝቦችን የገና አከባበር እና ለዘንድሮ ገና የወጡ አዳዲስ ዝማሬዎችን ይዘዋል፤ ያዳምጧቸው፡፡
XS
SM
MD
LG