በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን ሊቀ-ጳጳስ አቡነ ፍራንሲዝ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት


የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን ሊቀ-ጳጳስ አቡነ ፍራንሲዝ “ለከተማውም ለዓለምም” ሲሉ ባስተላለፉት የዕለተ-ገና መልዕክታቸው መጭው ዓመት በሁሉም ሃገሮችና ባሕሎች ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች መካከል የወንድማማችነት ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን ሊቀ-ጳጳስ አቡነ ፍራንሲዝ “ለከተማውም ለዓለምም” ሲሉ ባስተላለፉት የዕለተ-ገና መልዕክታቸው መጭው ዓመት በሁሉም ሃገሮችና ባሕሎች ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች መካከል የወንድማማችነት ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።

እንዲህ ዓይነቱ ግንኙነት በእሥራዔላዊያንና በፍልስጥዔማዊያን መካከል፤ በሶሪያና በየመንም ሰላም ያወርዳል የሚል ተስፋ እንዳላቸው አቡኑ ገልፀዋል።

“ለመልካም ገና ያለኝ ምኞት የወንድማማችነት ምኞት ነው” ብለዋል አባ ፍራንሲዝ በዓለም ዙሪያ ላሉ ከሚሊዮን በላይ ለሆኑ ካቶሊክ አማንያን ከቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ መቅደስ ባስተላለፉት መልዕክታቸው።

“የተለያየዩ ዕምነቶችና አመለካከቶች ባሏቸው መካከል ወንድማማችነት እንዲወርድ፣ አንዱ ሌላውን እንዲያከብርና እንዲደማመጥ፤ በሁሉምና በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ሰዎች ሁሉ ወንድማማች እንዲሆኑ እመኛለሁ” ብለዋል አቡነ ፍራሲዝ አክለው።

“መዳን የሚገኘው እጅግ በበዛ የዘር ዓይነት፣ ቋንቋዎች፣ ባሕሎች ለምንጋራው ለእኛ ምስኪን ሰብዕና ፍቅርን፣ መቀበልን፣ ማክበርን በማውረድ እንደሆነ የእግዚአብሄር ልጅ ነግሮናል፤ እኛ እኮ በሰውነታችን ሁላችንም ወንድማማችና እህትማማች ነን” ብለዋል አቡነ ፍራንሲዝ።

አቡኑ አክለውም “ልዩነቶቻችን እንቅፋትና አደጋ ሳይሀኑ የካብታምነት ምንጭ ናቸው” ብለዋል ለአማንያኑ ባስተላለፉት መልዕክታቸው።

የሰማንያ ሁለት ዓመቱ አቡን ነገም እንዲሁ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ፣ ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ ሰዓታት እንደሚቆሙ፣ በአዲሱ ዓመትም በቫቲካን አደባባይ ቁጥሩ ለበዛ ምዕመን ፀሎትና ቡራኬ እንደሚያደርጉ የተጣበበው የሣምንቱ መርኃግብራቸው ያሳያል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG