በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምሥራቅ ኢትዮጵያ ኮሌራ ሕይወት እየቀጠፈ ነው


 ፎቶ ፋይል፦ የኮሌራ አምጭ ሕዋስ - ትንሹ አንጀት ውስጥ
ፎቶ ፋይል፦ የኮሌራ አምጭ ሕዋስ - ትንሹ አንጀት ውስጥ

በከፍተኛ ጎርፍ በተጠቃው የምሥራቅ ኢትዮጵያ ክፍል፣ ኮሌራ የ23 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል ሲል የእንግሊዝ የሕፃናት አድን ድርጅት ዛሬ ሐሙስ አስታውቆ፣ ወረርሽኙ በቀጠናው ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቋል።

‘ኤል ኒኞ’ በተሰኘው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት፣ ኢትዮጵያ፤ ጎረቤቶቿን ኬንያን እና ሶማሊያን ጨምሮ በከፍተኛ ዝናብና ጎርፍ የተመቱ ሲሆን፤ በርካቶች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት፤ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል፣ 772 ሰዎች በበሽታው ሲያዙ፣ 23 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን እንዳጡ ድርጅቱ አስታውቋል።

በአስከፊ ሁኔታ በተጠቃው ቀላፎ አውራጃ፣ ከምስት ዓመት በታች በሆኑት ሕፃናት ላይ በፍጥነት በመዛመት ላይ ሲሆን፣ ይህም በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጠው 80 በመቶ መሆኑን ድርጀቱ ጨምሮ አመልክቷል።

የመጠጥ ውሃ ማጣሪያ እና የቧንቧ ውሃ በመበከሉ እንዲሁም መሠረታዊ የንፅህና መጠበቂያ አገልግሎቶች ባለመኖራቸው ገዳዩ በሽታ በፍጥነት ሊሰራጭ መቻሉ ተጠቁሟል።

በተበከለ ውሃ እና ምግብ አምካይነት የሚተላለፈው በሽታ፣ በኢትዮጵያ በ91 አካባቢዎች መከሰቱን ለማወቅ ተችሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG