በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናው ፕሬዚደንት የሩሲያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ተቀብለው አነጋገሩ


የሩሲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካሂል ሚሹስቲን የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ
የሩሲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካሂል ሚሹስቲን የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ

የሩሲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካሂል ሚሹስቲን ከቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ዛሬ ረቡዕ ቤጂንግ ውስጥ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በቻይና እና በሩሲያ መካከል ያለው የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥ መጠን እንደተቃደው በዓመቱ የመጀመሪያዎቹ 11 ወራት ውስጥ 200 ቢሊዮን ዶላር (USD) መድረሱ ተነግሯል፡፡

ይህም “በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ጠንካራ ጽናትና ሁለንተናዊ ትብብር ለማድረግ ሰፊ ተስፋን አሳይቷል” ሲል የመንግስት የዜና ወኪል ዢንዋ በስብሰባው ወቅት ሺ የተናገሩትን ጠቅሶ ዘግቧል።

ቤጂንግ ባለፈው አመት ከሩሲያ ጋር "ያልተገደበ" ወዳጅነት እንደነበራት አስታውቃለች፡፡

ቻይና ምዕራባውያን በሞስኮ ላይ የጣሉትን ማዕቀቦች አውግዛለች፡፡

ኔቶ እና ዩናይትድ ስቴትስ፣ በዩክሬን ውስጥ የሩስያ ወታደራዊ እርምጃ እንዲቀሰቀስ ካደረጉ በኋላ በዩክሬን ግጭት ውስጥ ራሳቸውን እንደ ገለልተኛ አካል አድርገው ለማቅረብ ይሞክራሉ ስትል ክስ ማቅረቧም ተመልክቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በመጋቢት ወር ሞስኮን የጎበኙ ሲሆን የሩሲያው ፕሬዚዳንት ፑቲን ባለፈው ወር የቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ መሠረተ ልማት ኢኒሼቲሽን ጉባኤ ላይ ለመካፈል ወደ ቤጂንግ መጓዛቸው ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG