በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሺ ለፑቲን ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ሞስኮን ይጎበኛሉ


የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግ
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግ

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግ ከመጭው ሰኞ አንስቶ እስከ ረቡዕ ድረስ ሩሲያን ለመጎብኘት አቅደዋል፡፡ ከዩክሬን ጦርነት ጋር ተያያዞ የምስራቁ ውጥረት እየከፋ ባለበት ወቅት ጉብኝታቸው ለሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ይመስላል ሲል አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

በዩክሬን የቀጠለው የሩሲያው ወረራ በፑቲን እና ሺ ንግግር ውስጥ ከፍተኛውን ሥፍራ ይይዛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቻይና የሞስኮን ጥፋት ለማውግዝ ፈቃደኛ አልሆነችም፡፡ ባላፈው ዓመት ከሩሲያ ጋር ያላት ግንኙነት “ያልተገደበ” መሆኑን በገለጸችበት ጊዜ ውስጥ እንኳ በግጭቱ ራሷን እንደገለልተኛ ወገን አስቀምጣለች፡፡

በሁለቱ አገሮች በሁለቱ መሪዎች መካከልክ የሚካሄደውን ስብሰባ ይፋ ያደረጉት ዛሬ ዐርብ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ቻይና፣ የሁሉም አገሮች ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት መከበር አለበት ብትልም ፣ ኔቶና ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያን ተንኩሰው ለወታደራዊ እርምጃ ዳርገዋል ስትል የምዕራባውያንን ማዕቀብ ተችታለች፡፡

ትናንት ሀሙስ፣ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኪን ጋንግ፣ ለዩክሬኑ አቻቸው ዲምትሮ ኩሌባ፣ ከቁጥጥር ውጭ የወጣው ግጭትን ቤጂንኝ ያሳሰባት መሆኑን ገልጸው ወደ አንድ ዓመት ግድም ስላስቆጠረው ግጭት የፖለቲካ መፍትሄ እንዲኖር ከሞስኮ ጋር መነጋገር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ኪን አያይዘውም “ቻይና ሁልጊዜ በዩክሬን ጉዳይ ተጨባጭና ፍትሃዊ አቋም አላት፣ ሰላምና ድርድር እንዲኖር ቁርጠኝነቱ ያላት ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ለሰላም ንግግር ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ጥሪ ታደርጋለች” ብለዋል፡፡ የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኩሌባ ቆየት ብለው ባስተላለፉት የትዊት መልዕክት፣ ኪን እና እሳቸው መነጋገራቸውን ጠቅሰው “ስለ ግዛት አንድነት አስፈላጊነት መወያየታቸውን” ገልጸዋል፡፡

ኩሌባ አክለውም “ዩክሬን ውስጥ የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆምና ሰላምን መልሶ ለማምጣት የሚያስፈልገውን (“የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለነስኪን”) የሰላም ቀመር አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥቻለሁ“ በማለት ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG