በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻያና ፕሬዚዳንት ስለሰሜን ኮሪያና ዩናይትድ ስቴትስ ስብሰባ ተግባራዊነት ተናገሩ

ሰሜን ኮሪያና ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ሳምንት ሲንጋፖር ውስጥ ባካሄዱት ታሪካዊ ስብሰባ የደረሱትን ሥምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚችሉ ተስፋ አለኝ ሲሉ የቻያና ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ ተናገሩ።

ሰሜን ኮሪያና ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ሳምንት ሲንጋፖር ውስጥ ባካሄዱት ታሪካዊ ስብሰባ የደረሱትን ሥምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚችሉ ተስፋ አለኝ ሲሉ የቻያና ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት ዛሬ ለሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ባደረጉት አቀባበል ላይ መሆኑን የቻይና መንግሥታዊ የዜና አገልግሎት ገልጿል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም የኮሪያን ልሳነ ምድር ሙሉ በሙሉ ከኒውክሊየር ነፃ ለማድረግ ሊሰሩ በለውጡ ፒዮንግያንግን ሲያስቆጣ የኖረው የዩናይትድ ስቴትስና የደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ልምምዶች በጊዜያዊነት እንዲቋረጡ ተስማምተዋል።

የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ የሁለቱ መሪዎች ጉባዔ ለኮሪያ ልሳነ ምድር የኒውክሊየር ጉዳይ ፖለቲካዊ መፍትኄ ለማግኘት ጠቃሚ ዕርምጃ ነው ማለታቸው ተጠቅሷል።

የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም የሁለት ቀናት ኦፊሴላዊ ጉባዔ ለማድረግ ቤጅንግ የገቡት ዛሬ ማክሰኞ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG