በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለመወያየት በዩናይትድ ስቴትስ የቀረበላትን ሃሳብ ተቀበለች


የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሉ ካኑ
የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሉ ካኑ

ቻይና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመወያየት በዩናይትድ ስቴትሱ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን የቀረበላትን ሃሳብ ተቀበለች፡፡

ቻይና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመወያየት በዩናይትድ ስቴትሱ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን የቀረበላትን ሃሳብ ተቀበለች፡፡

ከዚህ ሥምምነት የተደረሰው፤ በባሕረ ሠላጤው አካባቢ ያለው ውጥረት እያየለ በመጣበትና ይልቁንም የደቡብ ኮሪዊያው ፕሬዚደንት ኪም ጆንግ ኡን ቻይና ውስጥ የአራት ቀናት ጉብኝት በጀመሩበት ወቅት መሆኑም ታውቋል።

ዛሬ ረቡዕ በተጠራ ጋዜጣዊ ጉባዔ ላይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሉ ካኑ በሰጡት ቃል “ውጥረቱን ለማርገብና ድርድሩን ለማስጀመር ይቻል ዘንድ ቤይዢንግ ውይይቱን ትቀበላለች” ብለዋል።

በዚሁ ወቅት የዩናይትድ ስቴትሱ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን፣ ሰሜን ኮሪያ ወደ ድርድሩ ትመጣ ዘንድ፣ ቻይና ግፊት ማድረግ እንዳለባት አሳስበዋል።

አንድ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን ለቪኦኤ በሰቩት ቃል፣

“ሰሜን ኰሪያ ዝግጁ በሆነችበት በማናቸውም ጊዜ ለመወያየት፣ ውይይቱንም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለማድረግ ዝግጁዎች ነን” ማለታቸው ተሰምቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG