በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በዩክሬን ጦርነት ለማናቸውም ወገን የጦር መሳሪያ እንደማትሸጥ አስታወቀች


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኪን ጋንግ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኪን ጋንግ

ቻይና በዩክሬን ጦርነት ለየትኛውም ወገን መሳሪያ እንደማትሸጥ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኪን ጋንግ ዓርብ እለት አስታውቀዋል። ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ቤጂንግ ለሩሲያ ወታደራዊ እርዳታ ትሰጣለች ለሚለው የምዕራባውያን ስጋት ምላሽ በሰጡት ወቅት መሆኑን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል።

ቻይና በግጭቱ ገለልተኝነቷን ጠብቃ የቆየች ቢሆንም፣ ምዕራባውያን ሀገሮች ሩሲያ በጎረቤቷ ላይ ለፈፀመችው ወረራ ማዕቀቦችን በጣሉበትና ሞስኮን ለማግለል እየሞከሩ ባለበት ወቅት፣ ሩሲያን በፖለቲካ፣ በትርክት እና በኢኮኖሚ ስትደግፋት ቆይታለች።

ኪን ጋንግ ለሩሲያ የሚደረግ የጦር መሳሪያ ሽያጭን በተመለከተ እንዲህ ያለ ግልፅ መግለጫ የሰጡ ከፍተኛው የቻይና ባለስልጣን ናቸው። የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ቻይናን በመጎብኘት ላይ ካሉት የጀርመኑ አቻቸው አናሌና ቤሮቦክ ጎን ቆመው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ወታደራዊ ቁሳቁሶችን አስመልክቶ ቻይና ማስተዋልና ኃላፊነት ያለበት አቀራረብ ትከተላለች” ብለዋል።

ቻይና የጦር መሳሪያዎችን ለግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች አትሰጥም፣ ወደ ውጪ የሚላኩ ለሲቪልና ወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ መሳሪያዎችን ሽያጭ የምታከናውነውም በህጎች እና በደንቦች መሰረት ነው”

ኪን አይይዘውም “ቻይና የጦር መሳሪያዎችን ለግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች አትሰጥም፣ ወደ ውጪ የሚላኩ ለሲቪልና ወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ መሳሪያዎችን ሽያጭ የምታከናውነውም በህጎች እና በደንቦች መሰረት ነው” ብለዋል። ቻይና ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲመጣ ለማገዝ ፈቃደኛ መሆኗንም ሚኒስትሩ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ቢጂንግ እንደራሷ ግዛት የምትቆጥራትን ታይዋንን ለማስፈራራት ያካሄደችውን ከፍተኛ ወታደራዊ የጦር ልምምድ ተክትሎ በቀጠናው ለሚታየው ውጥረት፣ ኪን የታይዋንን መንግስት ተጠያቂ አድርገዋል።

በየካቲት ወር፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ቻይና ለሩሲያ የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶችን ለማቅረብ እያሰበች እንደሆነ የሚጠቁም መረጃ አሜሪካ እንደደረሳት ጠቁመው፣ በክሬምሊን ጦርነት ውስጥ እንደዚህ አይነት ተሳትፎ ማድረግ "ከፍተኛ ችግር" እንደሚፈጥር ገልፀዋል።

ከቅርብ ቀናት ወዲህ የአውሮፓ መሪዎች ቻይናን በጎበኙበት ወቅትም ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ ያወጡ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ፣ በወረራው ወቅት ቻይና ለሩሲያ የሰጠችው ድጋፍ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የገባችውን ቃል "በግልፅ የጣሰ ነው" ሲሉ ቁጣቸውን ገልፀዋል። የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም የቻይናን የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባልነት በመጥቀስ፣ ቻይና ግጭቱ እንዲቆም የማገዝ የተለየ ኃላፊነት አለባት ብለዋል።

XS
SM
MD
LG