በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ከዩናይትድ ስቴትስ ከምትገዛቸው ሸቀጦች ላይ ቀረጥ አቆማለሁ አለች

ቻይና እአአ በ2019 የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለሚቀጥሉት 90 ቀናት በ$126 ቢሊዮን ዶላር ከዩናይትድ ስቴትስ በምትገዛቸው ተሽከርካሪዎችና መለዋወጫዎች ላይ ቀረጥ አቆማለሁ ብላለች።

ቻይና እአአ በ2019 የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለሚቀጥሉት 90 ቀናት በ$126 ቢሊዮን ዶላር ከዩናይትድ ስቴትስ በምትገዛቸው ተሽከርካሪዎችና መለዋወጫዎች ላይ ቀረጥ አቆማለሁ ብላለች።

ሁለቱ የዓለማችን ኃያላን መንግሥታት መሪዎች፣ ፕሬዘዳንት ዢ ዪንፒንግ እና ዶናልድ ትረምፕ ከ10 ቀናት በፊት በመካከላቸው የተፈጠረውን የንግድ ንትርክ ለማቆም መስማማታቸው ይታወሳል።

ሁለቱ መሪዎች ቀረጥ ለማንሳት የደረሱት ሥምምነት፣ ጥሪያቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ተጨባጭ ዕርምጃ ነው ብላለች ቤጂንግ።

ድርድሮች እየተካሄዱ ባሉበት ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ቁሳቁሶች ላይ ግብር ላለመጨመር መስማማቷን፣ ፕሬዘዳንት ትረምፕ ቀደም ሲል መግለፃቸው ይታወሳል።

ቀረጦችን ለማንሳት በቻይናና ዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያሉ ዕቅዶች ከወጡ ወዲህ የዓለም ገበያ ሲዋዥቅ ከርሟል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG