በሃገራቸው የተጣሉ የምዕራባውያን ማዕቀቦች እና የንግድ ገደቦች እያየሉ በመጡበት ብሪክስ ራሱን ሁሉን አቀፍ አካል አድርጎ እንዲመሰርት እና አባል ሃገራት ከፍ ያሉ ኃላፊነቶችን እንዲወስዱ ቻይና ታሳስባለች ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዋንግ ዪ ዛሬ ማክሰኞ ተናገሩ።
በርካታ የቻይና ኩባንያዎች ሩስያ በዩክሬን የምታካሂደውን ጦርነት በመደገፋቸው ለምዕራባውያን ማዕቀብ ገጥሟቸዋል። ከዚህ በጨማሪ የአውሮፓ ኮምሽን በኢሌክትሪክ ኃይል የሚንቀሳቀሱ እና ረከስ ባለ ዋጋ የሚሸጡት አነስተኛ ቻይና ሰር አውቶሞቢሎች በአውሮፓ መኪና አምራቾች ላይ የሚያስድሩትን ተጽዕኖ ለመከላከል በያዝነው ሳምንት አዲስ የቀረጥ ድንጋጌ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ተጠብቋል።
የሰባቱ የዓለም ባለ ጸጋ አገራት ቡድን በያዝነው ሳምንት ‘ሩስያን ከምዕራባውያኑ ዓለም ማዕቀብ ተጽዕኖ እንድታመልጥ ለማድረግ እየረዱ ናቸው’ ያላቸውን አነስተኛ መጠን ያላቸውን የቻይና ባንኮች የተባሉትን ድርጊታቸውን እንዲያቆሙ የታለመ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ያስተላልፋሉ’ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሮይተርስ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ብራዚልን፣ ሩስያን፣ ህንድን፣ ቻይናን፣ እና ደቡብ አፍሪቃን፤ እንዲሁም ኢራንን፣ ግብጽን፣ ኢትዮጵያን እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስን ጨምሮ ዘጠኝ አባል አገራት ያሉት የምጣኔ ሃብት ሕብረት የሚንስትሮች ጉባኤ በሩስያዋ የኒዝኒ ኖቭጎሮድ በመካሄድ ላይ ነው።
መድረክ / ፎረም